“ኮሮናን ለመግታት በአዳማ ሰዎችን ከቤት ባትወጡ ይመከራል አልን እንጂ ግዳጅ አላደረግነውም ” የኦሮሚያ ጤና ቢሮ


በኮሮና ቫይረስ ሁለት ሰዎች ከአዳማ/ ናዝሬት ከተማ አስከአሁን መያዛቸውን መገኘቱን ተከትሎ የኦሮሚያ ጤና ቢሮ አዳማ ነዋሪዎችን ከቤት እንዳትወጡ በማለት ተነግሯል ተብሏል የተባለውን ወሬ ለማጣራት ፊደል ፖስት የክልሉን የጤና ቢሮ የኮሚኒኬሽን ሀላፊ ሲስተር ሰአዳ አህመድን ጠይቆ ነበር ።
ሲስተር ሰአዳ ሲመልሱ; ” እንደ አዳማ ብቻ ሳይሆን እንደ ኦሮሚያ ክልል የኮሮና ቫይረስን ስርጭትን ለመግታት አትጨባበጡ ፣ተሰብሳባቹ አትሂዱ፣እጃቹን በቀን ውስጥ ደጋግማቹ በሳሙና ታጠቡ ፣አስፈላጊ ጉዳይ ካልሆነ ከቤት አትውጡ አያልን ስፒከር እየያዝን ቀሰቀስን አንጂ ከቤት አትውጡ የሚል ግዳጅ ትእዛዝ አላስተላለፍንም ” በማለት ገልፃዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *