ክቡር ኮሌጅ ለዩንቨርስቲ ገቢ ተማሪዎችን የህይወት ክህሎት ስልጠና በነፃ ሰጥቷል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ  75  የመንግስትና ከግል  የመጡ  ከ500 በላይ ተማሪዎችን   በ አስራ አንድ ጉዳዮች ላይ በማተኮር  አንድ ነጥብ አምስት ሚልየን ብር በመበጀት የነፃ ስልጠና ሰጥቷል ።

የክቡር ኮሌጅ ፕሬዝዳንት
አቶ ደሳለኝ መኩሪያ  ባለፈው ቅዳሜ በአዶት ሲኒማ በነበረው ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ እንዳሉት  ተማሪዎች በኮሮና  ምክንያት ወደ ዩንቨርሰቲ የሚገቡ  ተማሪዎች ማ በህይወት ክህሎት ዙርያ ማግኘት ያለባቸውን ነገር   አላገኙም ብለዋል።

ተማሪዎቹ  በአመራርነት ፣በስራ ፈጠራነት፣  በሰሜት ብልህነት፣  በንግግር ክህሎት ፣በዌብ ዴቨሊፕመንት ፣ግራፊክስ ፣ ሮቦቶኪስ  በመሳሰሉት ዘርፎች ስልጠናም እንደወሰዱ አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል።
” እንደ ዜጋ ተማሪዎች መቀየር ሀገር መለወጥ ነው  ብለን እናምናለን። ቤተሰብ አካዳሚ የሚባል ት/ ቤት አለን ። የእኛን ተማሪዎች ብቻ ማሰልጠን  በቂ አይደለም ።  ምክንያቱም  ተማሪዎቻችን ዩንቨርስቲ ሲገቡ ብቻቸውን አይደለም ።ለዛም ነው   74 ት/ ቤት  ተማሪዎችን ጨምረን  ያሰለጠነው። ” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *