ከውጭ በሚመጡ ብዙ እቃዎች ላይ በዲያስፖራ አካውንት አስመጪዎች የውጭ ገንዘብ እንዳያገኙ እገዳ ተጣለ

በዲያስፖራ አካውንት ከግብርና ፣ከኢንደስትሪ ግብአትና ማሽነሪዎች ፣ከመድሀኒት፣የልጆች ምግብ እና የትምህርት መርጃዎች ቁስ በስተቀር ሌላ እቃ ከውጭ ማስመጣት አንደማይቻል ብሔራዊ ባንክ የካቲት 29,2013 ለሁሉም ባንኮች ባስተላለፈው ማስታወቁን ፊደል ፖስት መገንዘብ ችሏል።
ከውስጥ አዋቂዎች ፊደል ፖሰት በተረዳው መሰረት ለእገዳው መጣል ዋና ምክንያት በዲያስፖራ አካውንት ከፍተኛ መጠን ያለው የጥቁር ገበያ ገንዘብ እየተዘዋወረ በመሆኑና ይሄም የኢትዮጵያን ብር እያዳከመ የውጭ ምንዛሬ ገበያ የተረጋጋ አለማድረጉ ነው ተብሏል።
አዲሱ የእገዳ መመሪያ ምን አልባት ከውጭ እቃ የሚያስመጡ ሰዎች በዲያስፖራ አካውንት ከተፈቀዱ እቃዎች ውጪ የሚፈልጉትን እቃ ማስመጣት ስለማይችሉ የአቅርቦት እጥረት በገበያው ላይ ስለሚያጋጥም ገበያ ላይ ባሉት ወይንም ከውጭ በሚመጡ እቃዎች ላይ የዋጋ ንረት ሊያስከትል የሚችል ስጋት በነጋዴው ላይ ጭሯል።

በተቃራኒው መልኩ በዲያስፖራ አካውንት የውጭ ምንዛሬ የሚያገኙ ሰዎች ብሔራዊ ባንክ የከለከላቸውን እቃዎች ለማስመጣት ወደ ባንኮች ሄደው ወረፋ ስለሚጠብቁ ባንኮችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *