ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትናንት በአዲስ አበባ ላንድ ማርክ ሆስፒታል የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው?



ቄራ ገነት ሆቴል አካባቢ ላንድ ማርክ ሆስፒታል ትናንት መጋቢት 4,2012 ቀን ላይ አንዲት ከካናዳ በቅርቡ የመጣች ሴት እና ከዱባይ የመጣ አንድ ወንድ ኮሮና ቫይረስ ምርመራ አድርጉልን በማለት ወደ ላንድ ማርክ ሆስፒታሉ መምጣታቸውን ለፊደል ፖስት የዜና ዌብሳይት መረጃ ይደርሳል ።ፊደል ፖስትም ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ሆስፒታሉ ስልክ ቢደውል አይነሳም። ጉዳዪን ለጤና ጥበቃ ሚኒስትር ህዝብ ግንኙነት ፊደል ፓስት አሳውቆ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት የዌብሳይቱ ጋዜጠኛ ወደ ላንድ ማርክ ሆስፒታል አመራ ።
ጉዳዩ የሚመለከታቸው አስተዳደር ክፍል ሀላፊም አንዲት የሆስፒታሉን ሰራተኛ አስጠርተው ስለተፈጠረው ነገር የተጠራችው ሰራተኛ እንዲህ ብላ አስረዳች ።
” አንዲት ከካናዳ የመጣች ሴት የኮሮና ምርመራ ማድረግ እፈልጋለው ብላ መጣች ።እኛም ከየት እንደመጣች መች አዲስ አበባ እንደገባችም ነገረችን ።የኮሮና ቫይረስ መምርመርያ ባይኖረንም በሽታው የሚያሳያቸውን ምልክቶች ከአለባት ብለን መረመርን ።ምንም የለባትም ። ይህም ቢሆን መንግስት ጉዳዩን ማወቅ አለበት ብለን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሰዎችን ጠራን ።ሴትዯን ለብቻዋ አስቀመጥናት ። የመንግስት ሰዎች ለሁለት ሰአት ያክል ብንጠብቃቸው ሊመጡ አልቻሉም ። ለመንግስት ሰዎችም ሴትዮን ከፈለጉ ብለን የሴትዮን አድራሻ ሰጥተናቸው ።ሴትዬዋ ብቻዋን በመጣችበት መኪና ወደ ቤቷ ሄደች ።

” ከዛም ቀጠለ ።ጉሮሮዬን ይከረክረኛል ያለ ከዱባይ የመጣ ኢትዮጵያዊ ምናልባት ኮሮና ቫይረስ ይኖርብኝ ይሆን ብሎ መጣ ። ስንመረምረው የበሽታ ምልክቱ የለበትም ።ሆኖም የህብተረሰብ ጤና እንክባካቤ ሰዎች ጋር ደውለን ሰውዬው ከእኛ ከሄደ በኋላ መሀል መንገድ ላይ እንደተገናኙና የተለየ ነገር ካለ እንደሚያሳውቁን ነግረውናል ።” በማለት ስለተፈጠረው ነገር አስረድታለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *