የሴቶችና የልጃገረዶች ድጋፍ ኢትዮጵያ አምባሳደር ማህሌት ዘለቀ በዳግማዊ ሚኒሊክ ልጃገረድ ተማሪዎችን የወር አበባ ንፅህና አጠባበቅን በተመለከተ ትምህርትና ድጋፍ እያረገች ሲሆን የወር አበባ ሞዴስን በነፃነት መግዛትና ይዞ መንቀሳቀስ ኢትዮጵያ ወስጥ አሁንም ሴቶችን የሚያሳቅ ድርጊት ነው ብላለች ።
” ለብዙ ሴቶች የወር አበባ ሞዴስን መግዛት ስኳር እንደመግዛት በነፃነት የሚከነውን ተግባር አይደለም።ሀሸሽ እንደያዘ ሰው ሞዴሱን ደብቀን እንይዛለን። ስለ ወር አበባ በግልፅ ማውራት የተለመደ ተግባር አይደለም።ነውር ይመስል እንሳቀቃለን ። ስትል ለፊደል ፓስት ተናግራለች ።
” የአንድ ፓድ የሞዴስ ዋጋ አስከ 40 ብር ይደርሳል ።ብዙ ሴቶች በዚህ ምክንያት አንድ ንጥል ሞዴስን ረጅም ሰአት ይጠቀሙበታል ።ይሄ እራሱ የኢንፌክሽን ችግር ያመጣል ።” ስትል አስረድታለች
ማህሌት ተቀያሪ ፓንቶችን ያጡ ብዙ የሀገራችን ሴቶች አሉ ብላለች።
” አንድ ሚኒሊክ ት/ ቤት የሰማሁት ታሪክ አለ ።ልጅቷ አስተማሪያዋ ለትምህርት ማስተማርያ ብላ ያመጡትን ሳሙና ሰረቀች ።ከዛም መስረቋ ሲደረስባት ፓንቷን ማጠቢያ ሳሙና ስላጣች ሳሙናውን እንደሰረቀችው ተናገረች ።በገጠር የሀገራችን ክፍሎች ቅያሪ ፓንት ፣ማጠቢያ ሳሙና ያጡ ብዙ አሉ ።እንደሀገር ቆም ብለን አስበን ለዚህ መፍትሄ ማበጀት አለብን።” በማለት ተናግራለች
የኢኮኖሚክስ የመጨረሻ አመት ተማሪዋ ማህሌት በቀጣይ ከሚኒሊክ ት/ ቤት በተጨማሪ ሌሎች ት/ ቤቶች ላይ ተመሳሳይ ነገር ለመስራት እቅድ አውጥታ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን ተናግራለች።