እንደ ቻይናው አሊባባ ሻጭና ገዢን በኦንላየን የሚያገናኝ ትሬድ ኢትዮጵያ የሚባል ድርጅት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

በህገወጥ ደላሎች የሚፈጠረውን የእህል፣ የሸቀጦች ፣የእቃዎችን ዋጋ ለመቀነስ ሸማቹ ቀጥታ ከአምራቹና ከሻጩ ጋር የሚገናኝ የኦንላይ አሰራር ይዤ ቀርቢያለው ሲል ትሬድ ኢትዮጵያ የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት ዛሬ በኢሊሊ ሆቴል በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

የኦንላይን የአርስ በእርስ ገበያ ልውውጥ ፣ኦንላየን ቢዝነስ ዳይሬክተር ፣ኦንላየን ኤክስፖ፣አለም አቀፍ ጨረታ ፣ኦንላይን ስልጠና ፣ዲጂታል ማርኬቲንግ እና ዶክመንተሪ ጨመረሮ አንደሚሰራ የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ በርናባስ ወልደ ገብርኤል ኪዳኔ ተናግረዋል።
ገበሬዎች ፣ እቃና ምርት አስመጪና ላኪዎች ፣ስራ ፈጣሪዎች፣ ነጋዴዎች ፍብሪካዎች እና ሸማቾች www.tradethiopia.com ላይ በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ብለዋል።
” ገዢና ሻጭ በቀጥታ የሚያገናኝ ፕላትፎርም ሲኖር ሀብት አይባክንም ዋጋም ያለ አግባብ አይወደደም ።ጊዜና ጉልበት ይቀንሳል ።እኛም እሱን ነው እየሰራን ያለነው ” ብለዋል።
ደርጅቱ ከ30 በላይ ሀገሮችን በኦንላየን የመዘገበ ሲሆን ከ2,500 በላይ ምርትና አገልግሎቶች እንዲሁም ከአንድ ሚልየን በላይ የቢዝነስ ዳታ ቢዝ አንደመዘገበም ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *