በኮሮናቫይረስ ዙርያ በየቀኑ የአሀዝ መረጃ የሚለቀው በወርልዶሜትር ሰንጠረዥ መሰረት ኢትዮጵያ የኮሮና ምርምራ በስፋት ከማይደረግባቸው ሀገሮች አንዷ ስትሆን በዛሬው እለት በወጣው መረጃ ሀገሪቱ እስከአሁን ባለው ሂደቷ ከአንድ ሚልየን ሰዎች መሀል 284 ሰዎችን ነው በኮሮናቫይረስን ዙርያ የላብራቶሪ ምርምራ ያደረገችው ።
110,ሚልየን ህዝብ ባላት ኢትዮጵያ በሁለት ወር ውስጥ 32,689 ሰው የኮሮና ምርመራ ያደረገ ሲሆን ይሄም በቀን በአማካኝ ሲሰላ በቀን 545 ሰው ገደማ ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ምርመራ እየተደረገለት ነው ማለት ነው።
ከአንድ ሚልየን ሰው መሀል ጅቡቲ 15,537 ሰው ፣ኬንያ 577 ፣ደቡብ አፍሪካ ደግሞ 5,464 ሰው የኮቪዲ 19 ምርመራ አድርጓል።
በአለም ከአንድ ሚልየን ሰው መሀል ከ170,000 ሰው በመርመር ትልቁን ስፍራ የያዘችው አውሮፓዊቷ ፋሮስ አይላንድ ናት ።
ስፔን ከአንድ ሚልየን ሰው መሀል 52,781 ፣ጣልያን 41,584 አሚሪካ ደግሞ 25,584 ሰው እየመረመሩ መሆኑን የወርልዶሜትር የዛሬው መረጃ ያሳያል።