ኢትዮጵያና ሞሮኮ የማዳበሪያ ፕሮጀክት በድሬዳዋ ለማቋቋም ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ መንግስት በድሬዳዋ የማዳበሪያ ፕሮጀክት ለመተግበር ከሞሮኮ መንግሰት ባለቤትነት ከሚያስተዳድረው ፎስፌት ሮክ ማዕድን ማውጫ ፣ ፎስፎሪክ አሲድ አምራች እና ፎስፌት ማዳበሪያ አምራች ከሆነው ከኦ.ሲ.ፒ ግሩፕ ጋር የጋራ የልማት ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የተደረሰው አቶ አህመድ ሺዴ የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስትር ፣ እና ከኢትዮጵያ ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ፣ ከኢትዮጵያ ግብርና ቢዝነስ ኮርፖሬሽን እና ከኢትዮጵያ ማዕድን ፣ ነዳጅ እና ባዮፊውል ኮርፖሬሽን የተውውጣ ቡድን ናንዛሬ በሞሮኮ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነው።

በስምምነቱ መሠረት የአገር ውስጥ ሀብቶችን (የኢትዮጵያ ጋዝ እና ሞሮኮ ፎስፎሪክ አሲድ) በመጠቀም በድሬዳዋ የተቀናጀ የማዳበሪያ ፋብሪካ ይከፈታል።

ፕሮጀክቱ ዩሪያን እና ኤንፒኬ/ኤንፒኤስ ምርቶችን በማጣመር 2.5 ሚሊዮን ሚሊዮን ቶን የማዳበሪያ ማምረቻ ክፍልን ለማልማት በመጀመሪያው ምዕራፍ በግምት 2.4 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገው ሲሆን ይህም በዓመት 3.8 ሚሊዮን ቶን የማምረት አቅም ይኖረዋል። ሁለተኛው ዙር ደግሞ በአጠቃላይ 3.7 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ይፈልጋል።

በየጊዜው እያደገ የመጣውን የማዳበሪያ ፍላጎትን (በዋናነት ዩሪያ እና ኤንፒኤስ+) ለማሟላት ይህ ፕሮጀክት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። via MoFA

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *