አፍሪካውያን የክህሎትና የፈጠራ ባለሙያዎች ሽልማት ተካሄደ

አፍሪካውያን የክህሎትና የፈጠራ ባለሙያዎች የሚሸለሙበት ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ተካሄደ።

AFRICA OUTSTANDING PROFESSIONALS AWARD በሚል መጠሪያ በተለያየ የአህጉሪቱ ክፍል ለሚኖሩ የክህሎትና የፈጠራ ባለሙያዎች እንዲሁም ኢንተርፕርነርስ ሽልማት መሰጠት መጀመሩ አፍሪካን ወደተሻለ የኢኮኖሚ እድገትና የፈጠራ ባለቤትነት እንደሚያመራት ገለፃ ተደርጓል።

በሽልማት ስነስርዓቱ ሁለት ኢትዮጵያን ዶር አቤኔዜር ያእቆብ በሶፍትዌር ግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ፤ እና እንዳለ መኮንን የተባሉ በንግዱ ዘርፍ የተሰማሩ እንዲሁም ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የተመረጡ ቁጥራቸው የላቀ የፈጠራና ይክህሎት ባለሙያዎች በስነስርዓቱ ሽልማታቸውን አግኝተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *