አዲስ አበበ ኮሮና ቢያሰጋትም በግንቦትና በሰኔ በአመቱ ከፍተኛ የሆነ ጋብቻ በመዘጋጃ ቤት ተፈፅሟል


መጋቢት 4, 2012 ኢትዮጵያ የተከሰተው ኮሮናቫይረስ የብዙ ጥንዶችን ጋብቻ ያዘገያል ተብሎ ቢጠበቅም በግንቦትና በሰኔ ወራቶች በአመቱ ከፍተኛ የሆነ ጋብቻ መፈፀሙን ፊደል ፖስት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በ2012 ከመስከረም እሰከ ሰኔ ባሉ ወራቶቸ በሰኔ ወር የተመዘገበው የ 3,458 ጥንዶች ጋብቻ የአመቱ ትልቁን ቁጥር ሲይዝ ግንቦት ወር 2,871 ጥንዶችን በማጋባት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ቫይረሱ አዲስ አበባ የተከሰተበት መጋቢት ወር 2,367 ጥንዶችን በኤጀንሲው በኩል መጋባታቸውን በፊርማ ያረጋገጡ ሲሆን ሚያዝያ ወር 504 ጋብቻን በመመዝገብ የበጀት አመቱ ዝቅተኛ ጋብቻን ይዟል።

ለምን በኮሮና ወቅት ከፍተኛ ጋብቻ ተመዘገበ ?የሚለው ጥያቄ ጥናት ቢፈልግም የኤጀንሲው ሰራተኞች ግን ምን አልባት በኮሮና የሰርግ ድግስ ስለማይፈቀድ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ጥንዶች ኮሮናን አንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ቶሎ ፊርማ ተፈራርመው እየተጋቡ ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አስቀምጠዋል።

በበጀት አመቱ 28,984 ጥንዶች በኤጀንሲው የተረጋገጠ ጋብቻን ሲፈፅሙ አምና የነበረው ጋብቻ ደግሞ 25,241 አንደነበረ የኤጀንሲው መረጃ ያሳያል።
መረጃው በኤጀንሲው መጥቶ የተመዘገብን ጋብቻ
እንጂ በየቦታወ ኤጀንሲው ሳያውቀው የተፈፀመ ጋብቻን አያካትም ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *