አዛርባጃን ኤምባሲ ብሔራዊ ጀግናውን አስቦ ሊውል ነው


የአዛርባጃን ሪፐብሊክ ኤምባሲ የሃገሪቱ የምንጊዜም ምርጥ መሪ የሆኑትን የቀድሞ ፕሬዘዳንት ሀይደር አሊየቭ 98ኛ የልደት በዓል ሊያከብር ነው፡፡
እ.ኤ.አ ሜይ 1923 ዓ.ም በአዛርባጃኗ ናክቺቫን ከተማ የተወለዱት ሀይደር አሊርዛ ኦግሉ አሊየቭ ከ1993 እስከ 2004 ዓ.ም ሶስተኛው የሃገሪቱ ፕረዘዳንት በመሆን የመሩ ስመጥር ፖለቲከኛና ሃገር ወዳድ ነበሩ፡፡
የቀድሞው ፕሬዘዳንት አዘርባጃናዊያን ፈተና በገጠማቸው ጊዜ ድምጻቸውን ከፍ አርገው የሚያሰሙ ነበሩ፡፡ በቀድሞው የሶቭየት ህብረት አገዛዝ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስር ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር እና የኮሙኒስት ፓረቲ የሴንትራል ኮሚቴ ፖሊት ቢሮ አባል የነበሩ ቢሆንም አዛርባጃናውያን የሚደርስባቸውን ግፍና መጨቆን በመመልከት ከኃላፊነታቸው እስከመልቀቅ ደርሰዋል፡፡ በዚህም ሳይወሰኑ ጥቁሩ ጃንዋሪ በመባል በሚታወቀው እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 20 የደረሰውን ጭፍጨፋ በመቃውም መግለጫ አውጥተውም ነበር፡፡


ሀይደር አሊየቭ ሃገራዊ በሆነ ድጋፍ በምርጫ ወደ ስልጣን በመጡበት በኦክቶበር 3 1993  አዛርባጃን አደገኛ ውጥንቅጥ ውስጥ የነበረች የኢኮኖሚ አለመረጋጋት፣ በግዛት ምክንያት የተቀሰቀሰው ከአርሜኒያ ጋር የነበራት የማያባራ ጦርነት እንዲሁም በመላ ሃገሪቷ የተንሰራፉ ህገወጥ ቡድኖችን ጨምሮ ሃገሪቱ እልቆ ቢስ ችግሮች የተጋረጡባት ነበረች፡፡ ነገር ግን በእርሳቸው ብልህ አመራር በሃገሪቱ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ባህላዊ እድገቶች መመዝገብ ጀመሩ፡፡ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት አስገራሚ መሻሻል አሳየ፡፡ የነበራት ታማኝነት ስለጨመረም ወዳጆቿ መብዛት ጀመሩ፡፡
እንደ የአዛርባጃን ኤምባሲ ጉዳዮች ሥዩም እንደሆኑት አቶ ዲምተሪ ፓኒን ገለጻ ከሆነ የቀድሞው ፕሬዘዳንት ችግሮቹን በብልሃት ተጋፍጦ፣ ጠንካራ ሰራተኛ የሆነውን ህዝብ ፣ ወሳኝ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የነዳጅ ዘይት ክምችት እና የካስፒያን ባህር ንግድን ጨምሮ የነበሩበትን መልካም እድሎች በአግባቡ ተጠቅሞ አዛርባጃንን ከትቢያ ነበር ያነሳት፡፡


“አሁን ሃገሪቱ ጠንካራ ኢኮኖሚ አላቸው ከሚባሉ የቀድሞ የሶቬት ህብረት ሃገራት ተርታ የሆነች እና በክልሉ የቱሪዝም መናሀሪያ ነች,” ይላሉ ዲምተሪ ፓኒን፡፡  “ይህ የልደት በዓል የብሔራዊ ጀግናችን ሀይደር አሊየቭ ብቻ ሳይሆን የዘመናዊቷ አዛርባጃንም ልደት ነው ብለን ነው የምናምነው ፡፡” 
አቶ ዲምትሪ እንዳሉት አዛርባጃናዊያን በዚህ ወቅት የብሔራዊ ጀግናችንን ልደት ሲያከብሩ ልዩ ስሜት ይሰማቸዋል ምክንያቱም መሪያችን ለሃገራቸው ያለሙትና ያቀዱት ሁሉ ተሳክቷል፡፡ “አዛርባጃን ባለ ጠንካራ ኢኮኖሚ ሆናለች፡፡ ድንበሯ ተከብሮላታል፡፡” ብለዋል፡፡  
ድሚትሪ የሃገሩ ልጆች በተለይም ናጎርኖ ካራባክ እና በዚሪያው ያሉ የአዛርባጃን መሬቶች ከሦስት አስር ዓመታት በላይ በአርሜኒያ ወረራ ከተያዘበት ሙሉ በሙሉ ነጻ በወጣበት በዚህ ወቅት የታላቁን መሪያቸውን ልደት እንደማክበር ለእሱና ለሃገሩ ልጆች አስደሳች ነገር የለም ብሎ ያምናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *