አዛርባጃናዊ ኒዛሚ ጋንጃቪ መታሰቢያ የሆነ የግጥም ምሽት በአዲስ አበባ ተካሄደ

በአረቡ አለም ታላቅ የቅኔ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት አዛርባጃናዊ ኒዛሚ ጋንጃቪ መታሰቢያ የሆነ የግጥም ምሽት ባሳለፍነው በአዲስ አበባ ተካሄደ

ከ880 ዓመት በፊት ዝናው መላውን ዓለም ያዳረሰውን ይህንን ታላቅ ባለቅኔ የሚዘክረው ምሽት በርካታ ታዋቂ ወጣት ገጣሚያንን በማሳተፍ ባለፈው ሃሙስ ታህሳስ 21 ቀን 2001 ዓ.ም አዲስ አበባ ካዛንችስ አካባቢ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል ነበር የተካሄደው፡፡

በመድረኩ ላይ የባለቅኔው ስራዎች ተተርጉመው የቀረቡ ሲሆን የኒዛሚ ጋነጃቪ በተለያዩ የሚያ ዘርፎች ያበረከታቸው አስተዋፅኦዎችም ተተንትነዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኤምባሲ ጉዳዮች ተውካይ ሚ/ር ሩስላን ናሲቦቭ እንዳሉት ኒዛሚ ጋንጃቪ በዜግነት አዛርባጃናዊ ይሁን እንጂ ዝናውና አበርክቶው ከሀገሩ አልፎ መላው የአረብ ዓለም ላይ የናኘ ነው፡፡ እንደሳቸው ገለፃ ይህ የስነ ግጠም ምሽት በአዲስ አበባ የተካሄደው የአዛርባጃን ፕረዚድንት የተከበሩ ኢልሃም አሊየቭ በቅርቡ የተጠናቀቀው  እ.ኤ.አ. የ2011 ዓ.ም የኒዛሚ ጋንጃቪ ዓመት ተብሎ ሃገሪቱ እንዲሁም በመላው ዓለም በሚኖሩ አዛርባጃናዊያን ዘንድ እንዲከበር በውስኑት መሰረት ነው፡፡   

በአዛርባጃን ኒዛሚ ጋንጃቪን የሚዘክርና  የአዘርባጃን ብሄራዊ ገጣሚ የሆነበት ቦታ በጥብቅ ተመስርቷል. የዚህ ድንቅ ባለቅኒ ስምም በሁሉም ቦታ እና በሁሉም ነገር ላይ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *