አዘርባጃን ዳግም ነጻነቷን ያገኘችበትን 30ኛ ዓመት አከበረች


አዘርባጃን ነፃነቷን መልሳ የተጎናጸፈችበትን 30ኛ ዓመት ዛሬ አከበረች።
በ 19ኛው ክፍለ ዘመን የራሳቸውን ፍላጎቶች ለመጫን በተሰለፉባት የውጭ ኃይሎች እና ነጻ ሃገርነቷን ቢነፍጓትም በ20ኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ ላይ በአራቱም የአዛርባጃን ማእዘናት የሚገኙ ህዝቦቿ ብሄራዊ መነቃቃት በመፍጠር ለነጻነታቸው ተጋድለዋል። ይህ ተጋድሎ እ.ኤ.አ በ1918 አዛርባጃን ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን ወለደ።
በኢትዮጵያ የአዘርባጃን ሪፐብሊክ የኤምባሲ ጉዳዮች ተወካይ የሆኑት ሚስተር ሩስላን ናሲቦቭ እንዳሉት ይህም አዘርባጃንን በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ የመጀመሪያው ዓለማዊ ባለፓርላማ ዴሞክራሲያዊት ሃገር አድርጓታል። “አዘርባጃን እ.ኤ.አ. በ 1919 ለሴቶች የመምረጥ መብቶችን በመስጠት ብዙ የአውሮፓ አገሮችን እንኳን ትቀድማለች” ብለዋል ሩስላን።


የአዘርባጃን ህዝብ በሶቭየት ህብረት በግዳጅ እንዲቋጭ የተደረገውን የ1918-1920 የአዘርባጃን ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተተኪ የሆነውን የአዘርባጃን ሪፐብሊክን ጥቅምት 18 ቀን 1991 በመመስረት ነጻዋን አዛርባጃን እንደገና አስመለሰ።
“ነፃነትን መጠበቅ ከማግኘት የበለጠ ከባድ ነው” ብለው የሚያምኑት ሚስተር ሩስላን ናሲቦቭ በ20 ኛው ክፍለዘመን አዘርባጃን ሉዓላዊ ግዛት የመሆን ዕድል እንደነበራት ተናግረዋል። ሩስላን “የመጀመሪያው ዕድል ብዙም ሳይቆይ ተበላሸ” ብለዋል ሩስላን።
በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ግዛት ነፃነት ላይ የወጣው የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ከፍተኛ ምክር ቤት (ፓርላማ) መግለጫ ነሐሴ 1991 ተቀባይነት አገኘ ። ታሪካዊ የሆነው የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስብሰባ ደግሞ “ የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ግዛት ነፃነት ” በተሰኘው የሕገ -መንግስታዊ መመሪያን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 18 ቀን 1991 በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።


ሚስተር ሩስላን እንዳሉት የአዘርባጃን ነፃነት የተመለሰበት 30ኛ ዓመት ልዩ ነው ምክንያቱም በዓለም ዙሪያ ያሉ አዘርባጃኒያውያን የሃገራቸው የግዛት አንድነት ተረጋግጦ በድል አድራጊነት መንፈስ እያከበሩት ስለሆነ ነው።
ሩስላን “ፕሬዝዳንታችን እና ድል አድራጊው የሆኑት የጦር ሰራዊታችን ዋና አዛዥ ኢልሃም አሊዬቭ አንድ ጊዜ በግልፅ እንደተናገሩት የነፃነታችን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት በጣም ከባድ ነበሩ” ብለዋል። በአርሜኒያ ጠበኛ ፖሊሲ የተነሳ የእርስ በእርስ ጦርነት ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች እና ወደ 20% ገደማ የሚሆነው ግዛቶቻችን በወረራ መያዝ በጣም ፈታኝ ነበር። ሩስላን
“ብሄራዊ ጀግናችን ወደ ስልጣን መምጣት ተከትሎ አዘርባጃን ከአንዱ በቀር ሁሉንም ተግዳሮቶች በድል ተወጥታ ነበር። ዛሬ ግን ለአዛርባጃን ሰራዊት ክብር ይግባውና ቀድሞም የሃገራችን ግዛት የነበረው ወደፊትም ሆኖ የሚቀጥለው ካራባክ ክልል ከአርሜኒያ ወረራ ነጻ ስላወጣን ሁሉንም ተግዳሮቶቻችንን ድል ነስተናል” ብለዋል። “ሃገራችን ነጻነቷን ድጋሚ የተጎናጸፈችበትን 30ኛ ዓመት በምናከብርበት በዚህ ጊዜ ካራባክ አዛርባጃን ስለሆነ ሃገራችን ይበልጥ ነጻ ሆናለች።”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *