አውዳመት እና እናቴ

አውዳመት እና እናቴ

#ሰላም#EFDA#FIDEL

የሰው ሽር ጉድ ፤የገበያው ትርምስ ፤የሙዚቃው ጩኽት፤ የመኪናው ጡሩምባ
ብቻ ምን አለፋቹ የአውዳመት ዋዜማው ሁሉንም ቀልብ አሳጥቶታል
እንደሚመስለኝ ከእኔእና የእኔን መሳይ ችግር ከገጠማቸው ሰዎች በስተቀር
ሁሉም ሰው የአውዳመቱ ግርግር ተሳታፊ ነው፡፡
አንዳንዴ በደመነፍስ ልቤ ጥድፍ ይላል!
የሆነ የበአል እግጅት ውስጥ ያለሁ ይመስለኛል
ምን ዋጋ አለው አውዳመት እኛ ቤት ቀረ
የዛሬን አያድርገው እና አውዳመት እና እናቴ አመቱን ሙሉ ተገናኝተው የማያውቁ ይመስል
ግንኙነታቸው ሰርክ አዲስ ነው፡፡
አቤት ሩጫ….
አውዳመት ሲደርስ እናቴ የምትይዝ የምትጨብጠውን ታጣለች
የዶሮአይን የመሠለ ጠላ፤ዶሮው፤ዳቦው፤ጭሣጭሡ፤ቡናው
ውውይይ አውዳመት ….. ትዝታ ሆኖ ቀረ
የኔ ምስኪን እናት ያለችበት አካባቢ ሰላም ርቆታል ፡፡ አሁን እንዴት ሁና ይሆን ?
እንደእኔ የአውዳመቱን ሞቅታ ለማጣጣም ያልታደሉ
እንደ አይናቸው ብሌን የሚጠብቋቸው ቤተሰቦቻቸው እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያሉባቸው ሰዎች ቁጥራቸው ስንት ይሆን?
ህህምምም . . .
አውዳመት የሚደምቀው፤ወዳጅ ዘመድ የሚሰባሰበው፤ ደስታም ሆነ ሃዘን የሚታጀበው
ለካ ሁሉም ሠላም ሲሆን ነው!
ብቻ እስትፍፋሡዋ ስላለልኝ አምላኬን አመሰግነዋለሁ
በፈጣሪ ፍቃድ ሁሉም ነገር ሰላም ሁኖ የእናቴን አይን እስካይ ቸኩያለሁ
እስከዚያው ግን በእኔ እና እኔን መሰል ሰዎች ላይ የደረሰው ነገር
ድግግሞሹ በዝቶ ስር እየሠደደ ወላፈኑ ሌሎችን እንዳይፈጅ እዚህ ጋር ሊቋጭ ይገባል እና
ለምስኪን እናቶቻችን፤ ለእምቦቀቅላ ህጻናት፤ሰርተው ሃገር ማቆም ለሚችሉ አፍላ ወጣቶች፤መራቂ እና አስታራቂ ለሆኑ አዛውንቶች ሲባል
ሳንሰለች ስለ ሰላም እንምከር!

ትምህርት ለልማት ማህበር ወጣቶችን ወደ ሰላም አውድ ለማምጣት የሚሰራ ሃገር በቀል ድርጅት ነው ፡፡የመንግስት ሃላፊዎችን ከወጣቶች ጋር በማቀራረብ የማወያየት ስራን እየሰራ ነው ፡፡ በወለጋ ጊምቢ፣ነጆ እና ቅልጡ ካራ ወረዳዎችም ላይ ከ120 በላይ ወጣቶችን እና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ስለሰላም አወያይቷል ፡፡ ተሳታፊዎች ተቀራርበው እንዲሰሩ ድልድይ ሁኗል፡፡
ስለ ሰላም መስበክ ፣ስለሰላም መዘመር ፣ ለሰላም ዘብ መቆም የሁላችን የቤት ስራ ነውና ሁላችን እጅ በእጅ ተያይዘን ስለ ሰላም እንቁም ፣ ሰላም ለሁላችን ፣ሰላም ለሃገራችን ይሁን !!!!
ይህ መልዕክት የተላለፈላችሁ በትምህርት ለልማት ማህበር (Education For Development Association) ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *