በዓለም ግዙፉ የሆስፒታሎች አግልግሎት ሰንሰለት የቱርኩ አቺባደም ሄሌዝ ኬር ግሩፕ በኢትዮጵያ ተወካይ ጽ/ቤቱን ከፍቷል፡፡ በ 22 የተለያዩ ሀገሮች ውስጥ ከሚሰሩ 36 የጤና አገልግሎት ቢሮዎቹ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን ስለ አገልግሎቱ የምክር አገልግሎት የሚያገኙበትን አዲስ ቢሮ በአዲስ አበባ አስተዋውቋል፡፡ አቺባደም ሄልዝ ኬር ግሩፕ በእነዚህ የግንኙነት ጽ/ቤቶች አማካይነት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀን የጤና አገልግሎት ለኢትዮጵያዊያን ለማቅረብ ያለመ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡
አቺባደም ሄልዝ ግሩፕ በቱርክ ፣ መቄዶንያ ፣ ቡልጋሪያ እና ኔዘርላንድስን በመሳሰሉት ሀገሮች በሚገኙ 21 ሆስፒታሎች እና 13 የህክምና ማዕከላት የሚሰራ እና በዘርፉ ስመ ጥር ድርጅት ነው፡፡ አቺባደም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የምርመራ እና የሕክምና አገልግሎቶችን የላቀ ደረጃ ባላቸው ልዩ ባለሙያዎችና በተራቀቁ የቴክኖሎጂዎች በመታገዝ የሚያቀርብ ሲሆን በሌሎች ሀገሮች በሚገኙ የመረጃ መስጫ እና ማስተባበሪያ ማዕከሎቹ የሚሰጠውን ተቀራራቢ አገልግሎቶችም በኢትዮጵያ ጽ/ቤቱ ባለሞያዎች ይሰጣል፡፡
ታካሚዎች ከአገራቸው ሳይወጡ በአቺባደም ሆስፒታሎች የሚሰጠውን ተገቢ የምርመራ እና የሕክምና አገልግሎት አማራጮች በተመለከተ በቢሮዎች በመገኘት ሙሉ መረጃዎችን ዝግጁ ሆነው ከሚጠብቋቸው ባለሙዎች ማግኘት ይችላሉ፡፡ የሕክምና ሪፖርቶች እና የላብራቶሪ ምርመራዎች በተመለከተ በቱርክ ከሚመለከታቸው ሆስፒታሎች ጋር መረጃ መለዋወጥ እንዲሁም በአቺባደም ሐኪሞች በተሰጡ ምክሮች መሠረት ታካሚዎች ስለ ሕክምናው ዝርዝር መረጃ እንዲያገኝ ማድረግ አገልግሎቱ ከሚሰጣቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ህመምተኞች ወደ ቱርክ ለህክምና ሲጓዙ ሂደቱን ማስተባበር እና ከደረሱ በኋላም በኢስታንቡል አውሮፕላን ማረፊያ እና በሳቢሃ ጎኪን አየር ማረፊያ በሚገኙ የአቺባደም ሄልዝ ግሩፕ ቢሮዎች ተወካዮች አቀባበል ተደርጎላቸው ወደ ሆስፒታሎች ይዘዋወራሉ፡፡ በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የሕሙማን አገልግሎት ማዕከላት ህመምተኞች በምርመራ እና በሕክምና ሂደት ወቅት የጤና አጠባበቅ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሚስተናገዷው ሲሆን የአቺባደም ሆስፒታሎች ከ 22 ቋንቋዎችን ተናጋሪ በሆኑ ከ140 በላይ ተርጓሚዎች በመታገዝ ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟላበት አሰራር ተዘርግቷል፡፡
አቺባደም ሄልዝ ግሩፕ እ.ኤ.አ. በ 1991 እንደ አካባቢያዊ ሆስፒታል ሆኖ የተቋቋመ ሲሆን በጤና ክብካቤ አገልግሎት ውስጥ በተሳካ ሁኔታ እያደገ ሄዶ አገልግሎቱን አለም አቀፋዊ ለማድረግ የቻለ ግዙፍ ተቋም ነው። አቺባደም ሄልዝ ግሩፕ በ 22 አገራት ውስጥ በ 22 ሆስፒታሎች እና በ 18 የህክምና ማዕከላት በ 5 ሀገሮች የጤና እንክብካቤ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡ በሁሉም የጤና እንክብካቤ ዘርፎች ውስጥ “360-ዲግሪ” የአገልግሎት አቀራረብን በአጋር ኩባንያዎች በኩል ያቀርባል።
እ.ኤ.አ. በ 1991 የተቋቋመውን የመጀመሪያውን ሆስፒታል በመያዝ አቺባደም ሄልዝ ግሩፕ በአሁኑ ጊዜ በሆስፒታሎቹ እና በየሕክምና ማዕከላቱ 3500 ዶክተሮችን እና 4500 ነርሶችን ጨምሮ ወደ 22.500 ሠራተኞች በመያዝ የጤና ክብካቤ አገልግሎቶችን ይሰጣል። አቺባደም ለቴክኖሎጂው እና ለመሠረተ ልማት ምስጋና በተለያዩ ሆስፒታሎቹ እውቅና ባገኙ እና በተረጋገጡ የጤና ደረጃዎች መሠረት የምርመራ እና የሕክምና አገልግሎቶችን ያቀርባል። ከሆስፒታሎች እና የሕክምና ማዕከላት በተጨማሪ ለድጋፍ አገልግሎት በተጓዳኝ ኩባንያዎች በኩል በሁሉም የሕክምና ክፍሎች ውስጥ የተሟላ የጤና ክብካቤ አገልግሎቶችን ለታካሚዎች ይሰጣል።