አቶ አወሉ አብዲ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ



የብልጽግና ፓርቲ የውጭና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበሩት አቶ አወሉ አብዲ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው በመንግስት መሾማቸውን ፊደል ፖስት አረጋግጧል።

ዶክተር አብይ በሊቀመንበርነት የሚመራው ብልፅግና ፓርቲም በአቶ አወሉ ቦታ ሌላ ሰው ይተካል ተብሎ ይጠበቃል።

ባለፈው የካቲት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አማራ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትት የነበሩት አቶ ዮሐንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ሆነው ቢሾሙም ቦታውን አልፈልግም ማለታቸው ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *