ለ 13 አመት የቆዳ ህክምና የሰጠው አቤድ ሳር ቤት ሽመክት ህንፃ ላይ ሁለተኛ ክሊኒኩን ከፍቷል ።
አቤድ የቆዳ ህክምና ክሊኒክ አዲስ ባመጣሁት መሳሪያ የለምጥና እና የቆዳ ላብ ማጥፊያ ህክምና እየሰጠሁ ነውም ብሏል።
የክሊኒኩ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ድጋፌ ፀጋዬ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የቆዳ ህክምና አገልግሎት በኢትዮጵያ መሻሻል ቢያሳይም አገልግሎቱ ዝቅተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
ቤቴል ያለው ክሊኒካቸው አስራ ሶስት አመት አገልግሎት በሰጠበት ወቅት በፈንገስ፣በቫይረስ ፣ በፀሀይ እንዲሁም ደረጃቸውን ያልጠበቁ የውበት መገልገያ ምርቶች በመጠቀም ለቆዳ በሽታ የተዳረጉ ብዙ ሰዎችን እንዳከሙ ተናግረዋል።
አቤድ ክሊኒክም እየጨመረ የመጣውን የቆዳ ህመም ታካሚን አገልግሎት በስፋት ከመስጠት ቁጥር ሁለት ክሊኒክ በሳር ቤት ሽመክት ህንፃ እንደከፈተ ተናግረዋል።
አቤድ ክሊኒክ በለምጥ በሽታ ለተያዙ እንዲሁም የቆዳ ላብ ላስቸገራቸው ሰዎች ከበሽታቸው የሚድኑበት ዘመን የደረሰበትን የህክምና መሳሪያና አገልግሎት ከመስጠቱም ባሻገር ፀጉራቸው ለሳሳ እና ለሚነቃቀቀል እንዲሁም የእግራቸውና የእጃቸው ጥፍር ላይ መቁሰል ፣ማበጥና መድማት ላገጠማቸው ሰዎች ክሊኒኩ ህክምና እየሰጠ ነው ብለዋል።
የማህበራዊ አገልግሎት ግዴታን ከመወጣት አኳያ ክሊኒካቸው ለተወሰኑ ታካሚዎች የነፃ ህክምና ሰጥቷል እየሰጠ ይገኛልም ብለዋል።