አርክዉድስ የፊልም ኢንዱሰትሪውን የሚያነቃቁ አዳዲስ መርሃግብሮችን አስተዋወቀ


ፕሮግራሞቹም ዓመታዊ የፊልም ሽልማት፣የቀጥታ ፊልም ስርጭት አገልግሎትእና አዲስ የፊልም ከተማ ናቸው፡፡
በተጨማሪም ሙሉ በሙሉ ሃገራዊ የሆነ የቀድሞና የአሁን ኢትዮጵያዊ ፊልሞችን ብቻ በመረጃ መረብ አማካይነት ማሳየት የሚችልየቀጥታ ሥርጭት መድረክ አስተዋውቋል፡፡

አርክዉድስ በተጨማሪም የፊልም ከተማ ለመገንባት ቦታ መርጦ ለመረከብ ዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።የፊልም ከተማው ሲጠናቀቅ ጥራት ያላቸው የኢትዮጵያ ፊልሞችን ለመስራት የሚያስችሉ ዘመናዊ የፊልም መገልገያዎችና መሳሪያዎች የያዘ እና በአለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ ፊልሞችን መስራት የሚያስችል እንደሚሆን ተነግሯል። የፊልም ከተማው የፊልም ተሰጥኦ ያላቸው ፊልም መሥራት ያልቻሉ ወጣቶች የፊልም ሰሪዎች የፈጠራ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ሃላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡

ዛሬስራ የጀመረው የአርክዉድስ ዲጂታል የፊልም ማሠራጫ አዳዲስ እናየታዩ ፊልሞችን ሰንዶ የሚይዝ ሲሆን ኢትዮጵያዊ ፊልሞችን በአንድ ቦታ ለኢትዮጵያ ፊልም አድናቂዎች ማቅረብ እንደሚያስችል ተነግሯል።የቀጥታ ማሰራጫው ለኢትዮጵያ ፊልም አፍቃሪያን የፊልም ማሳያ መድረክ ብቻ ሳይሆን የባለሙያዎችን የቅጂ መብት የሚያስጠብቅና ፊልም ሰሪዎች ተገቢውን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆንንም ተወስቷል።
የአርክዉድ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ አርሴማ ወርቁ በምርቃ ቱ ላይ እንደተናገሩት ዛሬ የኢትዮጵያን የፊልም ኢንደስትሪ ሊለወጡ የሚችሉ ሶስት ፕሮግራሞችን ማስተዋወቅ በመቻላችን ለኢትዮጵያ ፊልም ኢንደስትሪ በጣምአስፈላጊ ቀን ነው፡፡ ዋና ስራ አስኪያጇ አክለውም “ለባለሙያዎችእውቅናየሚሰጥ፣ በየዓመቱ የሚካሄድ የፊልም ሽልማት ዛሬ ይፋ ስናደርግ ይህ ሽልማት ከእስካሁኖቹ ሽልማቶች ሁሉ በተለየ ፕሮዲውሰሮች፣ዳይሬክተሮች፣ጸሃፊዎች፣የቀድሞእና የአሁኖቹ የፊልም ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ይሸለሙበታል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *