አምነስቲ ኢንተርናሽናል በማይ ካድራ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ መገደላቸውን ገልፇል

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት በማይ ካድራ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ከሶስት ቀን በፊት በጅምላ መገደላቸውን ገልፇል

ግድያውንም የፈፀሙትን አካሎች መንግስት ለህግ እንዲያቀርብ ጠይቋል።
ግድያው ወደ ሁመራ መውጫ ባለ ስፍራ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካባቢ በሚገኝ ስፍራ መፈፀሙን በፎቶና ከአይን እማኞች አረጋግጫለው ሲል ሪፖርቱ ፅፏል።
ግድያ ምንም ፖለቲካዊ ቁርኝት በሌላቸው በቀን ሰራተኞች ላይ የተፈፀመ ሲሆን የግድያው እውነተኛ አጀንዳ ጊዜ ያወጣዋል ያለ ሲሆን መንግስት እያደረገ ላለው የሚሊታሪ ኦፕሬሽን ግልፀኝነት ሲባልና የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች በቀላሉ ለመስራት እንዲያግዝ በትግራይ የተቋረጠው የስልክና የኢንተርኔት ግንኙነት አንዲመለስ አምነስቲ የጠየቀ ሲሆን አምነስቲ በስፍራው የሚደርሰውን ማንኛውንም ኢ ሰብአዊ የመብት ጥሰትና ወንጀል እየመዘገብኩ ለአለም ህዝብ አጋልጣለው ብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *