ኔዘርላንድ የኢትዮጵያን የቅመማ ቅመም የውጭ ገቢ ለማሳደግ እያገዘች ነው

የኔዘርላንድ መንግስት ይፋ ባደረገው የአምስት ዓመት  እስትራቴጂ የኢትዮጵያን የቅመማ ቅመም  የውጭ ገበያ ለማሳደግ አልሟል

የኔዘርላንድ መንግስት ባ የታዳጊ ሀገራትን የውጭ ንግድ ለመጨመር  ባቀደው (Centre for the Promotion of Imports from developing countries (CBI)) በተባለው ፕርግራም  16 በኢትዮጵያ የሚመረቱ ቅመማ ቅመሞች ላይ  ትኩረት በማድረግ ለላኪዎች ድጋፍና ክትትል በማድረግ ሀገሪቱ ከውጭ የምታገኘውን  ገቢ ለማሳደግ  እየሰራ መሆኑን ዛሬ  በአዲስ አበባ በራዲሰ ብሉ ሆቴል በነበረ አውደ ጥናት ላይ ተገልፇል።

ከተመረጡት ቅመማ ቅመሞች ውስጥ  ኮረሪማ፣ ኮሰረት፣ ሚጥሚጣ እና ሌሎችም  ይገኙበታል።

ኔዘርላንድ ምክትል አምባሳደር ኢትዮጵያ  በዘርፉ የምታገኘው ገቢ በቂ አንዳልሆነ የጠቀሱ ሲሆን  ፕሮጀክቱ  በደንብ ከተተገበረ ኢትዮጵያ ቅመማ ቅመሞቿን ወደ አውሮፓ የተሻለ ገቢ ታገኛለች ብለዋል።

በቅርቡ በኢትዮጵያ ስታቲስቲካዊ አገልግሎት ያካሄደው የቅርብ ጊዜ የዳሰሳ ጥናት መሠረት ከ50 የተለያዩ የቅመማ ቅመም ዘሮች ኢትዮጵያ 240,000 ቶን ምርት የምታገኝ ሲሆን ነገር ግን ከ22.8 ሚሊዮን ሄክታር የግብርና  መሬት ውስጥ ለቅመማ ቅመም የዋለው አንድ ፐርሰንት ብቻ ነው። በዘርፉ  18 ሚሊዮን አነስተኛ አርሶ አደሮች  እየሰሩ ይገኛሉ።

ባለፈው ዓመት ከቅመማ ቅመም የውጭ ንግድ  17 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን በዘንደሮ በጀት 14 ሚሊየን የአሜሪካ  ዶላር ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ደበላ አዱኛ ዘርፉ  ብዙ ተስፋ ሰጪ ነገር ቢኖሩትም  ከውጭ  ንግድ የሚገኘው ገቢ አርኪ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
አቲ ደበላ “ብዙ መስራትና መድከም ብዙ ምርምርና ጥናት አንደሚያስፈልግም ” ተናግረዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *