ነዳጅ አዳዮች ከአንድ ሌትር የሚያገኙት ትርፍ ከ23 ሳንቲም ወደ 80 ሳንቲም እንዲያድግ መንግስትን ጠየቁ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር በዱቤ ነዳጅ እንዳንቀበል
መደረጉ አግባብ አይደለም ።መንግስት የትርፍ ህዳግ ሊጨምርልን ይገባል በማለት ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።
አሁን ባለው የ23 ሳንቲም የአንድ የሌትር የትርፍ ህዳግ አንድ ቦቲ መኪና ጭነት ለማራገፍ አንድ ነጥብ ሁለት ሚልየን ብር እናወጣለን ነገር ግን በዚህ ከአንድ ቦቲ መኪና ትርፋችን ከአስር ሺ ብር አይበልጥም በማለት ማህበሩ ቅሬታውን ገልፇል።

የነዳጅ አቅራቢዎ ኩባንያዎች ከመንግስት በዱቤ የሚቀበሉት ነዳጅ ከመጋቢት አንድ ጀምሮ በተዋረድ አየቀነሰ በሚቀጥለው አመት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ አንዲቀረ ሆኖ በመታቀዱ ነዳጅ አዳዮች ከነዳጅ አቅራቢዎች በዱቤ አንዳይቀበሉ ያደረገ ሲሆን ይሄም የተዳከመ የገንዘብ አቅም ላይ ሆነን በዱቤ አንደንገዛ መከልከላችን አግባብ አይደለም ሲሉ የማህበሩ አመራሮች ገልፀዋል።
በኮሮና እና በኢኮኖሚ ችግር ላይ ሆነን የመስሪያ ቦታችን ላይ አስከ 70 % የቤት ኪራይ ጭማሪ የነዳጅ ኩባንያዎች አድረገውባን ይሄም ንግዳችንን አዳክሞታል ብለዋል።

የመኪና ዘይት አቅርቦትም የተዳከመ በመሆኑ ዘርፉ በትልቅ ችግር ውስጥ ነው ብለዋል።

መንግስት ከነዳጅ ትርፍ ባታገኙም ከመኪና ዘይት ትርፍ ታገኛላቹ ቢልም የመኪና ዘይቱ የኪዎስኩ እንዲከፋፈል እየተደረገ ነዳጅ አቅራቢዎች በበቂ ዘይት እያገኘን አይደለም ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *