ባለፈው መስከረም ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩት የፈረንሳይ ባህል ሚኒስትር በኮሮና ቫይረስ ተያዙ



በፈረንሳይ መንግስት እርዳታ እየተዳሰ የነበረውን የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያንን ለመገምገም ባለፈው መስከረም ኢትዮጵያ የመጡትና ከጠ/ሚ ከዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ውይይት ያረጉት የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ፍራንክ ሬይስተር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል ።
የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቨር ቬራን ቢ ኤፍ ኤም ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት ” ሬይሰተር አሁን እቤቱ አረፍ ብሏል።ደህና ነው ።” በማለት ሚኒስትሩ እቤታቸው ሆነው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የ46 አመቱ ሬይስተር በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁት አምስት የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ከአንዱ ጋር በመገናኘታቸው ቫይረሱ ሊይዛቸው እንደቻለም ተነግሯል።
ሬይስተር ከፈረንሳይ ባለስልጣኖች መሀከል ግብረሰዶማዊ ነኝ በማለት በ2010 ዓ.ም መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን አጥብቀው ይደግፋሉ።

ሬይስተር ዛሬ ማክሰኞ ከፊልም ኢንደስትሪ ሰዎች ጋር እና ከአርቲስቶች ጋር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ ዉይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር።

በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 25 ሰዎች ሲሞቱ 1,412 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *