ባለፈው ሳምንት 200 ሙቀት መለኪያዎችን ለጤና ቢሮዎች ያስረከቡት በሆቴልና ኢንደስትሪ የተሰማሩት አቶ አይሸሹም በትውልድ ቀዬቸው ሰሜን ጉንደር ደንቢያ ወረዳ ቆላ ድባ ከተማ ለ200 አባወራዎች የስንዴ ዱቄትና የምግብ የዘይት ድጋፍ አድርገዋል።

የድጋፉ አላማ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሀገሪቱ ኢኮኖሚዉ ስለቀዘቀዘ አቅም የሌላቸውን አባወራዎች ለማገዝ ነው።
እርዳታውን የአቶ አይሸሹም ተካ እናት የሆኑት ወ/ሮ ስላስ ገብረመድህን ተወካይ በመሆን ለአባወራዎቹ አስረክበዋል።