ቢ.ጂ.አ.ይ ኢትዮጵያ ባለ ቡኒ ቀለሙን ” ዶፔል “ቢራን በገበያ ላይ አዋለቢ.ጂ.አ.ይ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ 5% የአልኮል መጠን ያለውን ” ዶፔል” የተባለ አዲስ ቢራን በኢትዮጵያ ገበያ ላይ ማዋሉን ለፊደል ፖሰት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከቢራ ባሻገር በድራፍትም መልክ ” ዶፔል ” እንደተዘጋጀ የተነገረ ሲሆን ከ 21 አመት በላይ ለሆኑ ሰዎች እንዲስማማ፣ በሙከራዎች እና የቀማሾች አስተያየት ታክሎበት የተጠመቀ መሆኑም ተነግሯል።

ሰሞኑን ወደ ገበያ የተቀላቀለው ይሔ ቢራ ጠንከር ያለ ጣእም ሲኖረው ከጉሮሮም ሲወርድ ቀለል ያለ ስሜት እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ቢራ በሚሸጥባቸው ኪዮስኮችና መጠጥ ቤቶች አንደሚገኝም ተገልፇል።

በቡኒ ቀለም ደረጃ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው “ዶፔል ” አንዱ ጠርሙስ 300 ሚሊ ሌትር የሚይዝ ሲሆን ለጠመቃ ከሚያስፈልገው ጥሬ ግብአት 50 ከመቶውን የሚጠቀመው በሀገር ውስጥ ምርት ነው ተብሏል ።
ይሄም ገብስ ለሚያመርቱ ገበሬዎች ተጨማሪ ስራ ገበያ ከመፍጠሩም ባሻገር ለሀገሪቷ ኢኮኖሚ ገንዘብና የስራ እድል አንደሚፈጥር ተጠቅሷል።

ቢ.ጂ.አ.ይ ኢትዮጵያ በፈረንሳዩ ካስቴል መጠጥ ካምፓኒ ስር ሆኖ የሚሰራ ሲሆን በኢትዮጵያ የቢራ ገበያ ሰፊ ድርሻ ያለው ኩባንያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *