ቢ.ጂ. አይ ኢትዮጵያና የኮምቦልቻ ሰራተኞቹ በጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች የብርና የብርድልብስ ድጋፍ አደረጉ

በኮምቦልቻ እና በደሴ ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች ቢ.ጂ. አይ ኢትዮጵያና አንድ ሚልየን ብር የሚያወጣ ብርድልብ ሰራተኞቹ ደግሞ 2 .2 ሚልየን ጥሬ ገንዘብ ሰጥተዋል።

ቢ.ጂ. አይ ኢትዮጵያና የኮምቦልቻ ፋብሪካ ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበር አቶ አልአዛር አሊ ባደረጉት ንግግር “የወገናችን መቸገር የእኛም መቸገር ነው ። ይሄን አይነት ድጋፍ ስናደርግ የአብሮ መኖራችን አንዱ እሴት ስለሆነ ነው ” ብለዋል።

የቢ.ጂ. አይ . ኢትዮጵያና የሰሜን ቀጠና ሽያጭ ሀላፊ አቶ ሲሳይ ጥላሁን ዛሬ ሰራተኞቹ ያደረጉት ድጋፍ የመጀመሪያ እንዳልሆነ ገልፀው ሰራተኞች ወገናቸው ሲቸገር መቼም ቢሆን ቆመው አንደማያዩ ገልፀው ተጨማሪ ድጋፍም ወደ ፊት በሌላ ቦታ ለተፈናቀሉት ወገኖች ይደረጋል ብለዋል።

የአማራ ክልል የተፈናቃዮች ገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተወካይ ቢ.ጂ. አይ ኢትዮጵያ በክልሉ ለሚከሰቱ ተፈጥሯዊም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎች ፈጥኖ በመድረስ ሀገራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ግንባር ቀደም ከሆኑ ድርጅቶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ይህ አሁን እያደረገ ያለው ተግባርም ቢ.ጂ. አይ . ኢትዮጵያ መቼም ቢሆን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ የህዝቡን ችግር ለማቃለል ከሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ አንዱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *