ቢጂአይ ኢትዮጵያ የሜታ ቢራን ግዥ አጠናቀቀ

ቢጂአይ ኢትዮጵያ የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ግዥ ለማጠናቀቅ ከኢትዮጵያ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ባለስልጣን ይሁንታን አገኘ።

ዛሬ ሚያዝያ 12 ቀን 2014 ዓ.ም በሰበታ ከተማ ሜታ አቦ በዲአይጆ እና በቢጂአይ አትዮጵያ መካከል ተፈርሞ የነበረው የግዥ እና ሽያጭ ስምምነት በኢትዮጵያ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ይሁንታን ማግኘቱ በሰበታ ከተማ፣ ሜታ አቦ በተዘጋጀ፣ የኦሮሚያ ክልል የሰበታ ከንቲባ፣ የሁለቱም ድርጅቶች ኃላፊዎች እና እና የሰራተኛ ማህበር አመራሮች በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮምያ ክልል የሰበታ ከተማ ከንቲባ “ካስቴል ግሩፕ በ2011 በባቱ ካስቴል ወይን ፋብሪካ መትከሉን አስታውሰው አሁን ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ለሁለተኛ ጊዜ ኢንቬስት በመድረጉ እጅግ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

ከንቲባዋ አያይዘውም “የኩባንያው ኃላፊዎች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ በማድረግ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያላቸውን እምነትና በማሳየታቸው ላመሰግናቸው እወዳለሁ።” ብለዋል
የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ላውረን ሌኩየ በበኩላቸው። “በዚህ በቢጂአይ ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ክስተት በሆነው የርክክብ ስነስርዓት አካል በመሆኔ ክብር ይሰማኛል። ለተደረገልን ፈጣንና ሙያዊ ድጋፍ ለኢትዮጵያ ንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣንን እና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ መንግስት፣ በካስቴል ግሩፕ እና በሰፊው የቢጂአይ ቤተሰብ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በከፍተኛ የችግር እና ፈታኝ ጊዜያትም ቢሆን ወገባቸው አስረው ቀንና ሌሊት በመስራት የድርጅታችን ስም ከፍ ባለበት እንዲቆይ ላደረጉት የቢጅአይ ሰራተኞች እና የቢጂአይ ቤተሰቦች ብሎም ለታማኝ ደንበኞቻችን እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ለዚህ ቀን አበቃችሁ። ከዛሬ ጀምሮ የታላቁ ቢጂአይ ኢትዮጵያ ቤተሰብነት ለተቀላቀላችሁ ለሜታ አቦ ቢራ ስራ አስፈፃሚዎች፣ ሰራተኞች፣ የሰበታ ማህበረሰብ እና አጋሮች እንኳን ደህና መጣችሁ። አብረን ሆነን ትልቁን ሜታ አቦ ቢራን ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ከፍ ብሎ ለማየት ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ቆርጬ የተነሳሁ መሆኔን ስነግራችሁ በከፍተኛ ደስታ ነው።” ብለዋል።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ አዲሱን የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ሲቀላቅል አሁን ያለውን የማምረት አቅም ከ 520ሺ HL ወደ 64000 ሺ HL እንደሚያሳድገው ተገልጿል።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ከ1998 ጀምሮ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ካስቴል ኩባንያ ቡድን የኢኖቬሽን መርህ አካል በመሆን ለሀገር እድገት ትልቅ አስተዋፅዖ እያደረገ ይገኛል። ቢጂአይ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ውስጥ መንቀሳቀስ ከጀመረ ጀምሮ የፋብሪካዎቹን ቁጥር እና መዳረሻዎቹን በፍጥነት በማስፋፋት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአሁኑ የሜታ ፋብሪካ ሲጨመር የስድስት ቢራ ፋብሪካዎች እና አንድ አልኮል የሌለው የማልት መጠጥ በተጨማሪም ኢትዮጵያን በዓለም የወይን ካርታ ላይ ያስመዘገበበትን የካስቴል ወይን ፋብሪካ ከፍቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *