የአዳማ/ ናዝሬት ተወላጅ የሆነችው የ27 አመቷ የድህረ ምረቃ ተማሪ ምርምር በምታደርግበት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ትምህርት ላብራቶሪ ክፍል ውስጥ ሞታ እንደተገኘች ፊደል ፖስት ከሆስፒታሉ የየስራ ሀላፊዎች አረጋግጧል።
ሐይማኖት በዳዳ የተባለችው ይህች ወጣት የድህረ ምረቃ ትምህርቷን ለማጠናቀቅ ባቀረበቸው ጥናት ላይ በላብራቶሪ ውስጥ ጥናት ላይ አንደነበረችም ታውቋል።
ትናንት ግንቦት 18,2012 አመሻሹ ላይ በላብራቶሪ ክፍሉ ውስጥ ሞታ እንደተገኘች የተገለፀ ሲሆን ፖሊስ አስከሬኗን ወስዶ ከተማሪዋ ሞት ጀርባ ማን እንዳለ ለማወቅ ምርመራ እያደረገ ነው ።
ሆስፒታሉ “ፓሊስ ምርመራ ላይ ስለሆነ ” በማለት በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።
ሀይማኖት የመጀመርያ ዲግሪዋን በፋርማሲ ትምህርት ከሚዛን ቴፒ ያገኘች ሲሆን በዛው ዩንቨርስቲ ረዳት አስተማሪ ሆናም ሰርታ ነበር።
ሚዛን ዩንቨርስቲ ላይ የዋንጫ ተሸላሚ ነበረች።