በደስተኛነት ደረጃ ኢትዮጵያ ከ146 ሀገሮች ተወዳድራ 131ኛ ደረጃ አግኝታለች።

የተባበሩት መንግስታት ዘላቂ ልማት መፍትሔዎች አውታረ መረብ አስረኛውን ዓመታዊውን የዓለም ደስታ ሪፖርት ባለፈው  እሁድ ያሳተመ ሲሆን ኢትዮጵያ  ከ146 ሀገሮች  ተወዳድራ  131ኛ ደረጃን በማግኘት ዝቅተኛ ውጤት አግኝታለች።

ማውሪሸስና  እና አይቮሪ ኮስት  በሪፖርቱ መሰረት  ከአፍሪካ ብዙ ደስተኛ  ሰው የሚኖርባቸው ሀገረት በመባል ቀደሚ ስፍራን ይዘዋል።

ማውሪሸስ፣ ሊቢያ እና አይቮሪ ኮስት በአለም አቀፍ የደስታ ቀን ይፋ በሆነው የአለም የደስታ ሪፖርት ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገራት ናቸው።

  ሪፖርቱ  ደስተኝነትን  ለመለካት  6 አመላካቾች ላይ ;   አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት በነፍስ ወከፍ ያለው ድርሻ ፣ ማህበራዊ ድጋፍ፣ ጤናማ የህይወት ዘመን፣ ነፃነት፣ ልግስና እና የሙስና ደረጃ ማተኮር የነበረበት ሲሆን ከዛ ይልቅ የደረጃ አሰጣጡ የተንጠለጠለው  በግለሰቦች የህይወት ምዘና ላይ ነው። ከአለም   ፊንላንድ፣ ዴንማርክ እና ስዊድን ከፍተኛ 3 ቦታዎችን ይዘዋል። 
አፍጋኒስታን የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች ።።የደስታ ደረጃው የባለፉት  የሶስት አመት አማካኝ ላይ የተመሰረተ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *