በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት የአዲስ አበባው የፋሲካ ኤክስፓና ባዛር መክፈቻ ለሳምንት ተራዝሟል



ሴንቸሪ ፕሮሞሽን በ29 ሚልየን ብር ጨረታ ያሸነፈበትና በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማእከልና የገበያ ልማት ድርጅት ላይ ለማዘጋጀት ደፋ ቀና ሲል የነበረበት የፊታችን መጋቢት18 ተከፍቶ እሰከ ፋሲካ ዋዜማ ድረስ ሊካሂድ የነበረው “አዲስ ኤክስፓ 2020” ኤክስፓና ባዛር መክፈቻ ለአንድ ሳምንት መራዘሙን አዘጋጆቹ ለፊደል ፖስት ገልፀዋል።
የሴንቸሪ ፕሮሞሽን ፕሮጀክት ሀላፊ ወይዘሪት እድላዊት ዘውገ ለፊደል ፖስት እንደገለፀችው ኤክስፓው መክፈቻ ማራዘም ያስፈለገበት ምክንያት ህዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ተመሳሳይ ነገር በመንግስት በመወሰዱ ነው ።
” ባዛርና ኤክስፓ ሰው የሚበዛበት ነው ።የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንዲህ አይነት ነገር ማከናወን ተጋላጭነትን ያመጣል። እኛም በአሁን ሰአት ይሄን ማድረግ አንፈልግም ።”
” የቫይረሱ ስርጭት ቆሞ ነገሮች መልካም ከሆኑና መንግስት ቀጥሉ ካለን ኤክስፓውን መጋቢት 25 ጀምረን እሰከ ዳግማዊ ትንሳኤ ድረስ እናከናውናለን ።ካልሆነም በየወቅቱ የደረሰንበትን አቋም ለነጋዴውና ለህብረተሰቡ እናሳውቃለን ” ብላለች ።
በብዙ መቶ ሺ ሰዉ ይጎበኘዋል ተብሎ የሚጠበቀው ኤክስፓ 450 የሚጠጉ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *