በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የስትሮክ እና የስፖይን ማዕከል ተከፈተ

ከደም ትቦ መዘጋት ፣ መርጋት እና መጥበብ ጋር በተያያዘ ሰውነታችንን መራመድ እስኪያቅተን ድረስ ስብርብር የሚያረግና በብዙ ሺ የሚቆጠር ኢትዮጵያውያንን በየአመቱ ለሞት የሚዳረግውን የስትሮክ በሽታን እዚሁ በሀገር ውስጥ ለማከም ከጓደኛቸው ጋር በመሆን አክሶን ስትሮክ እና የእስፖይን ማዕከል በአዲስ አበባ የከፈቱት ዶክተር ዶ/ር ወንደሰን ገ/ አማኑኤል ውጭ ለመታከም በሚልየን ብር ለሚከሰክሰው ታካሚ መልካም ነገር ይዘው መጥተዋል።

” በደም ግፊት እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች በተነሳ ከአርባ አስከ ስልሳ ባሉ እድሜ ላይ ብዙ የስትሮክ ታማሚዎች በሀገራችን እየታዩ ነው። ብዙዎች ህክምናውን ባለማግኘታቸው ሞተዋል ወይም የአልጋ ቁራኛ ሆነዋል። ይሄን ለማገዝ ከፈጣሪ እርዳታ ጋር ታግዘን የህክምና ማዕከል ከፍተናል። ይሄ ማዕከል በሀገራችን ከስትሮክ በሽታ ታማሚ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን አይደለም። ነገር ግን በተወሰነ መልኩም ቢሆን የተወሰኑ ታማሚዎችን ማከም እራሱ በራሱ ትልቅ ነገር ነው። ” በማለት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
ማዕከሉ 200 ሚልየን ብር እንደወጣበት ተገልፇል።
በኢትዮጵያ በስትሮክ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር በውል አይታወቅም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *