በአዲስ አበባ የወሲብ ንግድ በአመት በግምት ከ1.8 ቢልየን ብር በላይ ይንቀሳቀስበታል

በአዲስ አበባ የወሲብ ንግድ በአመት በግምት ከ1.8 ቢልየን ብር በላይ ይንቀሳቀስበታል

ፊደል ፖስት በአዲስ አበባ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ አሉ? አመታዊ ገቢያቸውስ ስንት ነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ባለ ድርሻ መስሪያ ቤቶችን ጠይቆ ነበር።

የመዲናዋ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የሴቶች ህፃናትና ወጣቶቸ ቢሮ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ወገኖችን ብዛት እና ገቢን በትክክለኛ ቁጥር ለማስደገፍ ከአቅም ውስንነት ምክንያት የዳሰሰ ጥናት ፈፅሞ አለማካሄዳቸውን ተቋማቱ ገልፀዋል።

የፌዴራሉ የኤችአይቪ መከላከልና ቁጥጥር ተቋም (ሀብኮ) በወሲብ ንግድ ላይ የጠራ መረጃ እንደሌለው ገልፆ፤ ከስድስት አመት በፊት ያካሄደው አጭር የዳሰሳ ጥናት መሰረት የከተማዋ የወሲብ ንግድ ተዳዳሪ ወገኖች ብዛት በቁጥር 17,790 በመነሻነት (Base Line) ለእቅድና ለስራ እንደሚጠቀምበት አስታውቋል ል።

ይሄን ቁጥር አንዳንድ መንግስተሰዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ሶሾሎጂስቶች የማይቀበሉት ሲሆን በሀገሪቱ ያለው ድህነት ፣ጦርነትና ፣የህዝብ ቁጥር መጨመር እና ስደት በአዲስ አበባ የሚሰማራውን የወሲብ ንግድ ተዳዳሪዎች ቁጥር ቢያንስ በትንሹ 50,000 እንደሚደርስ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።

ፊደል ፖስትም የሁለት አካሎች አማካኝ የሆነውን በከተማዋ ቢያንስ 34,000 ሴተኛ አዳሪዎች አንፃራዊ መነሻ በማስቀመጥ፤ የቀን ገቢያቸውን ለማወቅ ባደረገው በጣም አጭር የናሙና ጥናት አካሄዷል።

በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በወሲብ ንግድ የተሰማሩ እንስት ወገኖች በቀን ከሁለት መቶ እስከ 2,000 ብር ድረስ ገላቸውን በመሸጥ ኑሯቸውን ይመራሉ።

ይሄን አጭር ጥናት ንፅፅራዊ ስሌት በመጠቀም ፊደል ፖስት የወሲብ ንግድ ሰራተኞቹ በቀን 300 ብር በወር ደግሞ በአማካይ 15 ቀን ቢሰሩ ብሎ በማስላት፤ በወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ወገኖች አጠቃላይ ገቢ ከአንድ ነጥብ ስምንት ቢልየን ብር በላይ እንደሚዘዋወር የመጨረሻው ግኝቱ ያመላክታል።

በጥናቱ የተደረሰበት አንፃራዊ የገቢ ግኝት በአንድ ህጋዊ የንግድ ድርጅት የተሰበሰበ ገቢ ቢሆን፤ መንግስት ከአምስቶ መቶ ሚልየን ብር በላይ ቀረጥ ገቢ ሊሰበሰብ እንደሚችል ፊደል ፖስት ግምቱን አስቀምጧል።

በከተማ ሴተኛ አዳሪነት መንገድ ላይ ፣በመጠጥ ቤት ፣በማሳጅ ቤት፣ በጠላ ቤት ፣በጫትና ሽሻ ቤት ፣በመኖሪያ ቤት ፣በሆቴሎች ፣በትናንሽ ቆርቆሮ ቤቶች ውስጥ በብዛት የሚሰራ ሲሆን አሁን አሁን ደግሞ በቴልግራም ፣በፌስ ቡክ ፣በስልክ እና በደላሎች አማካኝነት ሴተኛ አዳሪዎቹን ከሚፈልጓቸው ወንዶች ጋር የማገናኘት ስራ ሲሰራ ይስተዋላል።

ከተወሰኑ አመታት በፊት በከተማዋ የሚገኙ ሴተኛ አዳሪዎች በብዛት ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚመጡ ሲሆን አሁን ከደቡብ የሀገሪቱ ክፍል ለዚህ ስራ የሚመጡ ሴቶች መብዛታቸውን ታዛቢዎች ይናገራሉ።

አቶ አበራ መላኩ የተባሉ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ ለፊደል ፖስት እንዳሉት በወሲብ ንግድ በእድሜም ከ16 አመት ጀምሮ ያለች ታዳጊ ሴት በስራው ተሰማርታ ሲታይ ድህነት ፣ የተበላሸ ትዳር ፣የተሻለ ብር አግኝቶ ቤተሰብን ለመርዳትና ለማጌጥ ፣ንቃተ ህሊና ማነስ በስራው ለመተዳደር የሚመጣውን ሴት ቁጥርን በየቀኑ እየጨመረው ይገኛል።

በኢትዮጵያ ገላን ሸጦ መተዳደር በህግ የተከለከለ ቢሆንም ሴተኛ አዳሪን ለማስቆም ከመንግስት እየተደረገ ያለ ጥረት ውስንነት እንዳለው ታዛቢዎች ያስረዳሉ።

የቅርብ አመታት ጥናት አንደሚያሳየው በአዲስ አበባ ከአራት የወሲብ ንግድ ሰራተኞች ውስጥ አንዷ ኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ አለ ተብሎ ይታመናል።

በሀገሪቷ በአሁኑ ወቅት ከ210,000 በላይ የወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሴቶች መኖራቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *