በአዲስ አበባ በወር በአማካኝ 20 አዳዲስ ፒንስዮኖች ይከፈታሉ።ቦሌና አቃቂ ከፍተኛውን ቁጥር ይዘዋል

ፊደል ፖስት ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ባገኘው መረጃ መሰረት በከተማዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ አዲስ 180 ፔንስዮኖች ወደ ስራ ገብተዋል ።

ይሄም በአማካኝ ሲሰላ በየወሩ በከተማው 20 አዳዲስ ፔንሲዮኖች ይከፈታሉ ማለት ነው ።
አብዛኞቹ ፔንሲዮኖቹ በፊት መኖሪያ ቤት የነበሩ ወይንም አዲስ በተገነባ ፎቅ ላይ ነው እየተከፈቱ ነው ያሉት ።
ከዋጋም አኳያ ለአጭር ጊዜ ቆይታ በአማካኝ ከ200 አስከ 600 መቶ ብር የሚያስከፍሉ ሲሆን ። ለአዳር ደግሞ ከአራት መቶ ብር እሰከ 800 ብር ያስከፍላሉ።

አዲስ ከተከፈቱት 180 ፔንስዮኖች ውስጥ 64ቱ በቦሌ ፣26ቱ በአቃቂ ፣20 ው ደግሞ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተከፈቱ ናቸው ።
በከተማዋ በአጠቃላይ 1,625 ፔንስዮኖች ሲኖሩ የከተማዋ ነዋሪ መብዛት ፣የመጠጥና የሴተኛ አዳሪዎች ቁጥር መጨመር ለፔንስዮኖቹ ቁጥር መጨመር ሚና ተጫውቷል።
ባለፈው አመት በአማካኝ በየወሩ 17 ፔንስዮኖች የተከፈቱ ሲሆን በየአመቱ በፔንስዮን የመኝታ አልጋ ለማከራየት ንግድ ፍቃድ የሚያወጡ ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *