በአዋሽ ባንክ ጠባቂ እግሩን የተመታው ወጣት ባንኩ የ2.5 ሚልዮን ብር ካሳ እንዲከፍለው ክስ መሰረተ

17 አመት በጀርመን የኖረውና ባለፈው አመት ህዳር 28 ,2012 አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ ጋር ባለ የኤትኤም ማሽን ብር ላወጣ ስል ከባንኩ ጥበቃው ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ግራ እግሬን በጥይት ተመትቻለው የደረሰበኝም ጉዳት ስራ እንዳልሰራ ከቤት እንዳልወጣ አድርጎኛል የሚለው ወጣት ኖቤል ነቢል አዋሽ ባንክ እና ወንጀል ፈፅሞብኛል ያለውን ጥበቃ 2.5 ሚልየን ብር ካሳ እንዲከፍሉት ክስ መመስረቱን ለፊደል ፖስት ገልፇል።

አቃቢ ህግ በባንኩ ጠባቂ ላይ የግድያ የወንጀል ክስ የመሰረተ ሲሆን የሶስት ምስክሮችም ቃል ዛሬ በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰማ ሲሆን የቀጣይ ሶስት ምስክሮችን ቃል ለመስማት ለግንቦት 19,2013 ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ ይዟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *