በአንድ ጠረጼዛ 20,000 ብር የሚያስከፍለው የልጅ ሚካኤልና ኦሉሚዴ የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ይቀርባል

በአንድ ጠረጼዛ 20,000 ብር የሚያስከፍለው የልጅ ሚካኤልና ኦሉሚዴ የሙዚቃ ኮንሰርት ዛሬ ይቀርባል

የ65 አመቱ የኮንጎ ሶኩስ ዘፋኝ አንቶይን ክሪስቶፍ አጌፓ ሙምባ ኦሉሚዴ ሶኩስ ኮፊፋ(ኮፊፋ) ከኢትዮጵያዊው ታዋቂ ሪፐር ልጅ ሚካኤል ጋር 1,400 ሰው ይታደምመበታል በሚታደምመበት ዘ ክለብ በተባለ ቦሌ መድሀአኒያለም አካባቢ በሚገኝ መዝናኛ ቤት ዛሬ ምሽት አራት ሰአት ጀምሮ የሙዚቃ ኮንሰርት እንደሚያቀርቡ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

በኮንሰርቱ ለመታደም አምስት ሰው በሚያስተናግደው በአንድ ጠረጴዛ 20,000 ብር የሚያስከፍል ሲሆን እራትና መጠጥንም የመግቢያ ክፍያው ያስተናግዳል ተብሏል ።
ልጅ ሚካኤል በጋዜጣው መግለጫ ላይ እንደተናገረው ” በዚህ አይነቱ ኮንሰርት ኢትዮጵያውያን እና አፍሪካውያን ዘፋኞች መጣመራቸው ሀገራችንን በይበልጥ ያስተዋውቃል “ብሏል።

ኦሉሚዴ በበኩሉ ” ኢትዮጵያን በአየር መንገዷና በታሪኳ እናውቃታለን ።እዚህ መጥቶ መዝፈን ለእኛ ትልቅ ኩራት ነው ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *