በመጪው ማክሰኞ የአለም ህዝብ ቁጥር ከስምንት ቢልየን ያልፋል ተባለ

ኢትዮጵያ ለህዝብ ቁጥር መጨመር ከተወቃሽ ሀገሮች ውስጥ ናት –

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት

ህንድ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ አመት ከቻይና ትበልጣለች ተብሏል። ሪፖርቱ በተጨማሪም የአለም የህዝብ ቁጥር እድገት እ.ኤ.አ. በ2020 ከ1% በታች መውረዱን፣ ይህም ከ1950 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልፇል።

እ.ኤ.አ. በ2050 ከግማሽ በላይ ለሚሆነው የህዝብ ቁጥር እድገት ተጠያቂ የሚሆኑት ስምንት ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ ስትገኝበት ማለትም ኮንጎ፣ ግብፅ፣ኘ፣ ህንድ፣ ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን፣ ፊሊፒንስ እና ታንዛኒያ ተካተዋል።

የአለም ህዝብ ብዛት በፈረንጆቹ 2080 10.4ቢሊየን እንደሚሆን ይገመታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *