በሀዋሳ ከአስር ሰው አንዱ ኮሮናቫይረስ እየተገኘበት ነው

የሲዳማ ክልል ዋና ከተማ የሆነችው ሀዋሳ ኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ አንደከሰተ ህብረተሰቡ ማስክና ፣ሳኒታይዘር እና እጅን ተደጋግሞ በሳሙና በመታጠብ የሚያደርገው ጥንቃቃቄ መልካም የነበረ ቢሆንም አሁን ግን የሚደረገው ጥንቃቄ መቀነሱን ተነግሯል።

ፊደል ፖስት ባለፈው አርብ ወደ ሃዋሳ ተጉዞ ባገኘው መረጃ መሰረት በከተማዋ ከ16,500 በላይ የቫይረሱን ምርመራ ያደረገ ሲሆን እስከ አሁን ከ 1,600 በላይ ሰው ቫይረሱ የተገኘበት ሲሆን ይሄም ከአስር ሰው አንዱ ኮሮና እየተገኘበት መሆኑን ያሳያል።

386,000 ሰው የሚኖርባት ሀዋሳ እሰከ አሁን 22 ሰው በቫይረሱ አጥታለች ።
እንደከተማዋ ቢሮ ከሆነ በትራንስፖርት ላይ ተጥሎ የነበረው በግማሽ ተሳፋሪ የመጫን አገልግሎት በመነሳቱ አካላዊ አርቀትን መጠበቅና ማስክ ማድረግን መተው በከተማዋ ላይ በተለይም በከተማዋ ገጠራማ አካባቢዎች እየተስተዋለ መሆኑን ለፊደል ፖስት ቢሮው ገልፇል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *