ቃጠሎ ደርሶባት የነበረው የስልጤዋ ቂልጦ ማርያም ገዳም ታድሳ ለአገልግሎት ክፍት ሆነች

ከአዲስ   አበባ  በ221 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኘው ቂልጦ ቅድስት ማርያም ገዳም  ከሰባት ወር በፊት  በግለሰቦች
ተቃጥላ የነበረ ቢሆንም   ትናንት እሁድ የኢትዮጵያ  የኦርቶዶክስ  ተዋህዶ አባቶችና  የኢትዮጵያ የእስልምና  ዕምነት  አባቶች በተገኙበት   ዳግም  አገልግሎት  ጀምሯለች ።

የሁለቱም ዕምነት አባቶች በየትኛውም ዕምነት ያለ ተንኳሽ ተግባራትን  ምዕመናንም ፣ሰባኪዎች ፣አባቶች የሚመለከተው ሁሉ  አጥብቆ  ሊዋጋው ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያን ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ በምርቃቱ ላይ የተገኙ ሲሆን  በሀይማኖት ሰበብ ዕምነት ተቋምን ማውደም  የትኛውም ዕምነት የሚደግፈው ተግባር አይደለም ብለዋል።

” ከዚ በኋላ  መስጂድ ሲቃጠል ህዝበ ክርስቲያኑ አዳነው ቤ/ ክ ሲቃጠል  ህዝበ ሙስሊሙ አዳነው  የሚል ዜና ብቻ  ነው መስማት  ምንፈልገው ።” ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *