የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ፍትህ ወ/ሰንበትን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አድርጎ በድጋሜ መርጧል።

የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ምርጫ ያካሄደ ሲሆን አቶ ፍትህ ወ/ሰንበትን በድጋሚ ለአራት አመት እንዲሩ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል።ጉባኤው የቀረቡትን አጀንዳዎች መሠረት በአደረገው ውይይት የክለቦች ቁጥር እንዲጨምር መደረጉ ፣ በአህጉር አቀፍ ውድድሮች በመሳተፍ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ ፣ የሴቶች ሻምፒዮና ራሱን ችሎ መካሄድ መቻሉ በጥንካሬ አንስቷል ።

በሌላ በኩል የዳኞች እና የአሰልጣኞች ብቃት ማሳደግ ላይ ትኩረት ተሰጦት ሊሰራ እንደሚገባ ፣ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር እንዲጀመር እና የክለቦች ቁጥር እንዲጨምር ፌዴሬሽኑ ሊሰራ እንደሚገባ ጉባኤው አሳስቧል ።

በኢትዮጵያ አስተናግጅነት በቀጣይ በሚካሄደው 2020 ዞን 5 ቻሌንጅ ትሮፊ ውድድር በብቃት ለማስተናገድ እና ውጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት ሊደረግ እንደሚገባ ጉባኤው አቅጣጫ አስቀምጧል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *