“ሴቶችን ማገት ሀገር ማገት ነው ” ስለታገቱት ተማሪዎች በጎንደርና በሌሎች ከተሞች ሰልፍ ተካሂዷል።

“ሴቶችን ማገት ሀገር ማገት ነው ” ሰለታገቱት ተማሪዎች በጎንደርና በሌሎች ከተሞች ሰልፍ ተካሂዷል።
በደምቢዶሎ ዪንቨርስቲ ይማሩ የነበሩ እና ከሁለት ወር በፊት ወደቤት ሲመለሱ እስከአሁነ ማንነታቸው ባልታወቀ ቡድኖች ስለተጋቱት 17 የአማራ ክልል ተማሪዎች መንግስት ከእገታው እንዲያስለቅቃቸው ለማድረግ ዛሬ ጥር 24 ከጠዋት አንድ አሰአት ጀምሮ በጎንደር ፣በደብረ ታቦር ፣በዋግኅምራ እና በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው ።ሴቶችን ማገት ሀገር ማገት ነው ፣ሴቶቻችን ይለቀቁ ፣ሴቶች ሚኒስትሮች የት አላቹ? የሚሉ መፈክሮች በሰላሚዊ ሰልፉ ላይ ታይተዋል። ከታዳጊ ተማሪዎች አንስቶ ወጣቶች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣አዛውንቶች እና ጎልማሶች በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተሳትፈዋል።ከቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት በተሰጠ መግለጫ የታገቱት ተማሪዎች በሒወት እንዳሉ ቢገለፅም ለጥንቃቄ ሲባል የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የተነገረ ነገር የለም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *