ራይት ራይድ የሜትር ታክሲ አገልግሎት በ4,000 መኪኖች ስራ ጀመረ

በ 9919 የስልክ ጥሪ የሜትር ታክሲ ትራንስፖርት ፈላጊዎች አገልግሎት የሚያገኙበት ራይት ራይድ የሚባል የሜትር ታክሲ ዛሬ አገልሎቱን በይፋ ጀምሯል።

በእይታ ቢዝነስ ሶሊዩሽን ሃ/የተ/የግ/ማ አቅራቢነት በዛሬው እለት በይፋ በአዲስ አበባ ስራ የጀመረው ራይት ራይድ (RR) ከ4000 በላይ አሽከርካሪዎችን በአባልነት መያዙ ተነግሯል ።

የእይታ ቢዝነስ ሶሉሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ሁሴን እንደተናገሩት አገልግሎቱን ተጠቃሚዎች ከዛሬ ጀምሮ ራይት ራይድ የተሰኘውን የሞባይል መተግበሪያ ከፕሌይ ስቶር በማውረድ ወይም በ 9919 ላይ በመደወል አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።

የሞባይል መተግበሪያው ትእዛዝ ከመቀበል ባለፈ የአሽከርካሪውን ደህንነት የሚያሳውቅ የአስቸኳይ ጊዜ የአደጋ ጥሪ ገጽታ እንዳለው ተገልጿል ።

በ5 በመቶ  የኮሚሽን ክፍያ አገልግሎት እንደሚሰጥ ያስታወቀው ድርጅቱ ለቀጣዮቹ ሶስት ወራት ያለ ኮሚሽን ክፍያ እንደሚሰራ ገልጿል ።

የመነሻ ዋጋው 50 ብር ሲሆን በኪ.ሜ 12 ብር እንደሚያስከፍል ታውቋል።
እንዲሁም ራይት ራይድን የሚጠቀሙ አሽከርራካሪዎች የመኪና እጥበትና አገልግሎትን የመኪና ዘይትን ግዢን በተወሰነ ቅናሽ ያገኛሉ ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *