“ሥልጣንን ያለ ህዝብ ምርጫ ለማራዘም ሲባል ሕገ መንግሥቱን መጣስ ህሊናዬ አይፈቅድልኝም” ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም

ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤነት መልቀቃቸውን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሥልጣንን ያለ ህዝብ ምርጫ ለማራዘም ሲባል ሕገ መንግሥቱን መጣስ ህሊናዬ አይፈቅድልኝም ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

የሕገመንግሥት ትርጉም የሕገመንግስቱን መንፈስ ለመተርጎም እንጂ አዲስ ህግ ለማውጣት አይተረጎምም፣ መንግሥት ሥልጣኑን ለማራዘም አማራጭ የፈለገበት መንገድ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የፌዴሬሽኑን ሥልጣንና መብት በተጋፋ መልኩ ውሳኔው ቀድሞ የተወሰነ ነው ‘ከዚህ ውጪ ወየውላችሁ’ የሚል መግለጫም ተሰጥቷል የሚሉት ወ/ሮ ኬሪያ ይህም ታሪካዊ ሥህተት ነው፡፡ ውሳኔውም የምክር ቤቱ እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የምሑራን አይደለም ብለዋል፡፡

እኔ ሙስሊም ወጣት ሴት ሆኜ የወጣቶችን ነፍስ የታደገውን፣ የሃይማኖት እኩልነት ያረጋገጠውን ሕገመንግስት መጣስ ስለማልፈልግና ሕብረ ብሔራዊ ሥርዓትን አደጋ ላይ የሚጥል አንባገነናዊ ሥርዓት ለመቀበል አልፈልግም፣ አልተባበርም፣ አልፈጽምም ሲሉ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *