ምርጫ ቦርድ የአቶ አየለ ጫሚሶ ቅንጅት በሀሰተኛ አባል ፊርማ አጭበርብሮኛል አለ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአቶ አየለ ጫሚሶ የሚመራው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ በአዲሱ አዋጅ በተደነገገው መሰረት 7,214 ተጨማሪ መስራች የፓርቲ አባላትን አስፈርሞ እስከ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ እንዲያቀርብ ተገልጾለት የነበረ ቢሆንም ቦርዱ ከእያንዳንዱ ገጽ ላይ በተወሰደ እና ወካይ ሊሆን የሚችል ናሙና ባደረገው ማጣራት፣ ጥሪ ካደረገባላቸው 50 ፈራሚዎች መካከል፣ አንዱ ብቻ ፈርሞ ሲገኝ 49ኙ ግን በተለያየ ምክንያት ፊርማቸውን አለማኖራቸውን አረጋግጫለው በአብዛኛው የተሳሳተ ስልክ አና አልፈረምኩም የሚሉ ምላሾችና የማይሰራ መስመር ሆነው ተገኝተዋል ሲል በይፋዊ ፌስ ቡክ ገፁ አሳውቋል።

ፓርቲው ጥር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከ8 ክልሎች የተሰበሰበ የመስራች አባላት ፊርማ የያዘ ሰነድ ለቦርዱ ቢያቀርብም የፓርቲው ማመልከቻ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ቢፈርሙም፣ የተሰበሰበው ፊርማ ቃለ መሃላ ላይ የፈረመው ሌላ ግለሰብ መሆኑንና ሃላፊነቱም አለመገለጹን አስታውቋል።
የአያት ስም ያላስመዘገቡ፣ ስለአባልነታቸው በፊርማቸው ያላረጋገጡ፣ እድሜ፣ ጾታ፣ የምዝገባ ቀናቸው የማይታወቅ ፈራሚ ስሞችም በጉልህ ተገኝተዋል ሲል ቦርዱ ገልፇል

በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና አዋጁን ለማስፈጸም የወጣው አዋጅ መሰረት በአባልነት ያልተመዘገበን ሰው የተመዘገበ በማስመሰል የሌለን ሰው እንዳለ ማስመሰል ሃሰተኛ ስምና ፊርማ ማዘጋጀት በጥብቅ የተከለከለ ስለሆነ የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ጉዳዩን ተመልክቶ ህጋዊ ማጣራት እንዲያደርግ ዛሬ አመልክቻለው ብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *