መሀን ሆኖ ሺ ልጆች መውለድስ እንደ እ-ዳ-ዬ! !

መሀን ሆኖ ሺ ልጆች መውለድስ እንደ እ-ዳ-ዬ! ! ዶ/ር አበበች ጎበና ሰው በጠፋበት ዘመን ሰው ሆነው የተገኙ ልበ ቀና !!

በአበበች ጎበና ትምህርት ቤት አለመግባት ሊያሾፍ የፈለገ ስሙንም ድርጅቱንም መጥቀስ የማልፈልግ አንድ የአለም አቀፍ ድርጅት የኢትዪጵያ ቅርንጫፍ ሀላፊ እሱ የሚሰራበት ድርጅት የአፍሪካ ተወካይ ሀላፊ ሲመጣ ወደ ጨው በረንዳ አካባቢ ወደ ሚገኘው የአበበች ጎበና ድርጅትን ያመጣዋል ።

የአፍሪካ ተወካዩ አሮጊቷ አበበች በሚሰሩት ነገር ተደንቆ ስለ ሚረዷቸው ፣ስለሚያስድጓቸው ፣ስለ ሰራቸው ት/ ቤቶች ገለፃ ከተደረገለት በኋላ የኢትዮጵያ ተወካዩ አንዲህ አለው ” ሳይማሩ እንዲህ የሰሩ ትንሽ ፊደል ቢቆጥሩ ምን አንደሚሰሩ እንደሚችሉ አስበከዋል? ” አለው ።
የአፍሪካ ተወካዩም ” ቢማሩ አንደ አንተ ይሆኑ ነበር ” በማለት ተምርያለው ብሎ በመኮፈስ በተግባር የሚታይ የአበበች አይነት ስራ አለመስራቱን ለመንገር በቅኔ ነገረው።

እስቲ ከእኛ ውስጥ ስለሚሰራው መልካም ስራ ከሚስቱ ወይም ከባሉ ተፋቶ ስራውን የመረጠ ማን አለ?

ደግ ስራቸው የክብር ዶክተር ያሰጣቸው ዶ/ር አበበች ግን አርገውታል።
የዛሬ 41 አመት ግሸን ማርያም ተሳልመው ሲመጡ በርሃብ የመነመኑ ልጆችን ለማሳደግ አዲስ አበባ ይዘው ሲመጡ ባለቤታቸው ዞር በይ ” አንቺ ሴትዮ እብድ ነሽ መሰለኝ ” በማለት ባላቸው ሲፈቷቸው የተራቡ ልጆችን ሜዳ ላይ ከመተው ባላቸውን መፍታት መርጠዋል።

እስቲ ከእኛ ውስጥ መሀን ሆኖ ልጅ ስጠኝ ከማለት ተርፎ የተቸገረ ልጅ አምጥቶ የሚያሳድግ ማን አለ?

የብዙዎቻችን ምርጫ ልጅ ከሌለን ልጅ ስጠን ብለን ፈጣሪን ስንማፀን አንውላለን እንጂ ወላጆቹ የሞቱ ወይም የተቸገረ አንድ ልጅ አምጥተን ለማሳደግ ድፍረት እና ቀና ልብ ያንሰናል ።

ዶ/አበበች ግን አርገውታል ። በሁለት ልጅ ጀምረው ከአራት ሺ ልጆች በላይ ከውጭም ከሀገር ውስጥ የእርዳታ ብር እየጠየቁ አሳድገው ፣ትምህርት አስተምረው አስመርቀዋል።

በቅፅል ስማቸው እ-ዳ-ዬ! ተብለው በሳዳጓቸው ልጆች የሚጠሩት አበበች መሀን ነኝ ብለው ልጅ ከመውለድ አልተቆጠቡም ።ሊያውም ሺ ዎችን ወልደዋል ።
አበበች ጋር ልጅ ለማግኘት ዘጠኝ ወር ተፀንሶ ከመሀፀን መውጣት የለበትም ። “ስንት የተቸገረ ልጅ እንደማሳደግ ምንድን ነው መሀን ነኝ ብሎ ማላዘን ” በማለት የሚናገሩት
እ-ዳ-ዬ ሺ ወልዶችን ወልደው ሺ ዎችን ለቁም ነገር አብቅተዋል። በእሳቸው ድርጅት ቴክኒክና ሙያ ተምረው ዛሬ ሱቅ ከፍተው ንግድ ስራ የሚሰሩ ብዙ ናቸው።
ሲወለዱ መንገድ ላይ ተጥለው አበበች ጠጡ አጥብታ ያሳደገቻቸው ዛሬ አግብተው ወይም ስራ ይዘው የተለወጡትን ቤት ይቁጠረው።
ሰው መቼም ከመስራት ይልቅ መኮንን ይወዳልና አንዳንድ የሰፈራቸው ሰዎች ” መርጠው ነው የሚረዱት ” በማለት አሮጊቷን መጥፎ ስም ለማላበስ ሲሞክሩ ይታያል።
” የእኛ ሰው አስቸጋሪ ነው ። አንድ ሺ ሰው ለመረዳት ቢመጣ አንድ ሺ ሰው የመርዳት አቅም አይኖረኝም ። ያልተረዳው ሰው ሊከፋው ይችላል ።አቅም ሲገኝ እረዳለው ስል መርጠሽ ነው የምትረጂው የሚል ስም ይሰጠኛል ። ይሁን ግድ የለም የተረዳውም ሰው የቸገረው ነውና ብዙም አልከፋም ።ባሌም ሰው ለምን ረዳሽ አይደለም ብሎ ተከፍቶ የፈታኝ ።የሰውም ሀሜት ምንም አይመስለኝም ” ይላሉ ስለሚወራባቸውን ስም ማጥፋት መልስ ሲሰጡ።
እ-ዳ-ዬ እራስ ወዳድ አይደለችም ያላትን ነገር ስታካፍል ፈጣሪ የልቧን መልካም ሀሳብ በሺ አብዝቶ የሰው ፍቅር የሰጣት ናት ።
ቤቷን ወደ ህፃናት ማሳደጊያ የቀየረች ለምትጠቀምባቸው የቤት እቃዎች ግድ የሌላት በድሮ ሶፋ ፣በድሮ ትሪ ፣በድሮ ልብስ የምትኖር ልቧ የተቸገርን በመርዳት ሀሴት የሚያደርግ የብዙ ሺ እናት ናት ።
መሀን ሆኖ ሺ ልጆች መውለድስ እንደ እ-ዳ-ዬ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *