ሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ 40 ሚለየን የፊት ጭንብሎችን ለተማሪዎች ሊያከፋፍል ነው

በኮሮናቫይረስ ምክንያት ተዘግተው በቅርቡ ለሚከፈቱት የኢትዮጵያ ት/ ቤቶች ሐዋሳ ኢንደስትሪ ፖርክ 40 ሚለየን የፊት ጭንብሎችን ለተማሪዎች በቀጣይ ሁለት ሳምንት ውስጥ አምርቶ ለማከፋፈል እየሰራ መሆኑን የፓርኩ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍፁም ከተማ ለፊደል ፖስት ተናግረዋል።
ለተማሪዎቹ የሚከፋፈሉት ጭንብሎች አንዱ ቢያንስ ለሀያ አምስት ጊዜ ታጥቦ ማገልገል እንደሚችል ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ 25 ሚልየን ተማሪዎች በአንደኛ ፣በሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በመሰናዶ ት/ ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ሲሆን መንግስት ትምህርት በቀጣይ ሳምንታቶች ከመጀመሩ በፊት ኮሮናን ለመከላከል እንዲረዳ ለአንድ ተማሪ ሁለት ጭንብሎችን በነፃ እሰጣለው ማለቱ ይታወሳል።

በተመሳሳይ ሁኔታ አዳማ ኢንደስትሪ ፓርክም 10 ሚለየን የፊት ጭንብሎችን ለተማሪዎች በሁለት ሳምንት ውስጥ አምርቶ ለማከፋፈል እየሰራ መሆኑ ታውቋል።
በአጠቃላይ ሀዋሳ እና አዳማ ኢንደስትሪ ፓርኮች 50 ሚለየን የፊት ጭንብሎችን አመርተው ለተማሪዎች እንዲያከፋፍሉ ከመንግስት ትእዛዝ ተቀብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *