ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነው ተሾሙ


ቋሚ ሲኖዶስ ረቡዕ ኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሔደው ሳምንታዊ ስብሰባ ላይ፣ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በዕጩነት ቀርበው ከተመረጡ በኋላ፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ በተፈረመ ደብዳቤ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተሹመዋል፡፡

የሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን ሹመት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በጥቅምቱ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ነን” በማለታቸው ሥልጣነ ክህነታቸው ታግዶ ከነበሩት ጋራ በተደረገው ውይይት መግባባት ላይ በመደረሱ፣ ክህነታቸው የተያዘባቸው ካህናት ሥልጣነ ክህነታቸው ተለቆላቸው በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የሥራ መደብ ተሰጥቷቸው እንዲያገለግሉ የወሰነውን መሠረት የተሰጠ መኾኑ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *