ሉፍታንዛ ፣ገልፍ እና ኳታር አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ መብረር አቆሙ


አለምን እያመሰው ያለው ከቻይና ወሃን ተነስቶ ጣልያንና ኢራንን ጨምሮ በአለም ላይ ከ6,000 በላይ ሒወት የቀጠፈው የኮሮና ቫይረስ የብዙ አየር መንገዶችን በረራ አያሰረዘ ነው ።
በቦሌ አየር መንገድ ለረጅም አመት ከተለያዩ ሀገራት መንገፈኞችን ያርፉ የነበሩት አንደገና ጭነውም ወደ ተነሱበት ሀረገር የሚበሩት የጀርመኑ ሉፍታንዛ ኤርዌይስ ፣ የኳታር መንግስት ንብረት የሆነው ኳታር ኤር ዌይስ እና የባህሬኑ ገልፍ ኤር ወደ ቦሌ ኤርፓርት ከዛሬ ጀምሮ ለመጪው ሁለት ሳምንት እንደማይመጡ ፊደል ፖስት መረጃ ደርሶታል።

አየር መንገዶቹ በረራውን ያቆሙት በሀገራቸው የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት እንዲያግዛቸው በማሰብ ነው።
በትናንት ዘገባችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ጀምሮ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ወደ ሱዳን፣ግብፅ፣ ኬንያ ሊባኖስና ፈረንሳይና ኳታር የሚያደረገውን በረራ ላልተወሰነ ግዜ መሰረዙን መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *