የአዘርባጃን ኤምባሲ በተሻጋሪ ወንዙ ብክለት ላይ ያለውን ስጋት ገለፀ


በአዲስ አበባ የሚገኘው የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ኤምባሲ በአካባቢም ሆነ በሰው ልጅ ላይ ጉዳት እያደረሰ ባለው የቹቻይ ወንዝ ብክለት ስጋት እንደተስማው ገለፀ፡፡
የኤምባሲው ሻርጃ ዲ አፌር የሆኑት ሩስላን ናሲቦቭ እንደተናገሩት ከአርሜኒያ ወደ አዘርባጃን የሚያልፈው ቹቻይ ወንዝ እየተበከለ ያልው ካፓን ማይኒንግ እና ፕሮሰሲንግ ኮምቢን እና የዛንዙር ኮፐር ሞሊብዲነም ኮምባይን በተባሉ ሁለት አርሜኒያ ውስጥ በሚግኙ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ነው፡፡ “ወንዙ በእነዚህ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች በጣም ተበክሏል” ብለዋል ሩስላን ፡፡
በዚህ ዓመት ከጥር እስከ መጋቢት ባለው ጊዜ በተደረገ አንድ ጥናት መሠረት የከባድ ማዕድናት ከፍተኛ ይዘት ፣ በተለይም መዳብ ፣ ሞሊብዲነም ፣ ማግኒኖች ፣ ብረት ፣ ዚንክ እና ክሮምየም ወደ ወንዙ ገብቷል ፡፡ “ጥናቱ ያሳየን ነገር ቢኖር የወንዙ የብክለት መጠን ከሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች እጅግ የላቀ መሆኑን ነው” ብለዋል የኤምባሲው ጉዳዮች ሻርጃ ፡፡ እንደ ሩስላን ገለፃ ከሆነ ይህም በውስጡ የሚግኙ እንስሳትን ያጠፋል እንዲሁም የተበከለውን ውሃ መጠቀሙ ለጤንነት በጣም አደጋ ነው፡፡


ወደ 70 ከመቶው የአዘርባጃን የውሃ ፍጆታ የሚገኘው ቹቻይ ወንዝን ጨምሮ በአብዛኛው ከጎረቤት ሀገሮች ከፈሱ ወንዞቸ ከሚገኙ የገፀ-ምድር ውሃዎች ነው ፡፡ ወንዙ ለመጠጥ እና በአብዛኛው ለመስኖ አገልግሎት ይውላል ፡፡ ለቤት እና ለግብርና ሰራዎቸ የሚያገለግለው የዚህ ወንዝ መበከል እጅግ አሉታዊ ውጤቶችን ያስከትላል ፡፡ የወንዙ ቀለም ወደ ነጭ ወይም ወደ አሲድ ቢጫነት እንደተቀየረ እንዲሁም በአደገኛ ንጥረ ነገሮች ከመጠን በላይ በመከማቸት ከፍተኛ የሆነ የዓሣ ሞት እንደተከሰተ በርካታ የመገናኛ ብዙሃኖች ዘግበዋል፡፡
“በዚህ ምክንያት አርሜኒያ በምትወስደው በዚህ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያንን እና በአጠቃላይ አፍሪካውያንን ጨምሮ የአለም ማህበረሰብ ትኩረት እንፈልጋለን” ብለዋል ፡፡


ኩባንያዎቹ ያለ ምንም ህክምና በቀጥታ ቆሻሻቸውን ወደ ወንዙ በመጣል የአካባቢ ጥበቃ ግዴታዎችን ማክበር ባለመቻላቸው አርሜኒያም ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት በቸልተኝነት በመመልከቷ በአዛርባጃን እንዲሁም ሌሎች የካውካሰስ አካባቢዎች ላይ በሰው ልጆች እና አካባቢ ጥበቃ ላይ አደጋ እንዲደርስ በማድረግ ላይ ናቸው ፡፡ ይህም የሚያሳስበው የአዘርባጃንን ህዝብ እና መንግስት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያንና እና አፍሪካን ጨምሮ መላው የዓለምን አቀፍ ማህበረሰብ መሆን ይኖርበታል ”ብለዋል ፡፡
የውሃ ሃብት ከሚፈጥራቸው አልመግባባቶች ይልቅ የትብብር ምንጭ ሊሆን ይችላል ብለው እንደሚያምኑ ሩስላን ተናግረዋል ፡፡ “የሄልሲንኪ የድንበር ተሻጋሪ ውሃዎች ስምምነት በሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲፈርም ግፊት እያደረግን ነበር ፡፡”
አርሜኒያ የአካባቢውን ማህበርሰብ ትብብር ለማጠናከር፣ የአከባቢን እንክብካቤ ስራዎቸን ለማረጋገጥ እና የድንበር ተሻጋሪ የገፀ-ምድር እና የከርሰ ምድር ውሃ ጥበቃን ለማሳካት እኤአ በ1992 ዓም በፊንላንድ ለተፀነሰው ይህ ስምምነት ተገዥ ለመሆን አልፈረመችም ብለዋል ፡፡

One thought on “የአዘርባጃን ኤምባሲ በተሻጋሪ ወንዙ ብክለት ላይ ያለውን ስጋት ገለፀ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *