ሲኤን ኤን በሰሜን ኮርያ ዜጎች የሚተዳደረውን ኤንኬ የተባለ ድህረገፅን ጠቅሶ አንደዘገበው የ36 አመቱ የሰሜን ኮርያ መሪ መሪ ኪም ጂንግ ኡን ከሶስት ሳምንት በፊተ የልብ ቀዶጥገና ህክምና አርገው በፀና ታመው አንደነበረና በቅርቡም በአያታቸው ( የሰሜን ኮርያ መስራች በሆኑት ኪም ሰነግ ሁለተኛ ) ልደት ማስታወሻ ፕሮግራም ላይ ሊገኙ አንዳልቻሉ ዘግቧል።
በተጨማሪም ሀገሪቱ በቅርቡ ባስወነጨፈቻቸው ሚስየሎች ላይ ንገግር ሲያደርጉ አልታዩም ምክንያቱም በጠና ታመው ስለነበረ ነው በማለት ድህረ ገፁ ምክንያቱን ያቀርባል።
ከፍተኛ የሆነ የሲጋራ ሱስ ፣ወፍረት እና ከመጠን በላይ ስራ ማብዛት ጤናቸው ላይ ችግር መፍጠር ከጀመረ መሰነባበቱን ተነግሯል።
ከደቡብ ኮርያ ዋና ከተማ ሆኖ የሚሰራው ኤንኬ ዌብሳይት አንዳለው ኪም ማውንት ኩማንግ በተባለ ሪዞርት ህክምናቸውን ሲከታተሉ እንደነበር ጠቅሷል።
ስለ ሰሜን ኮርያ በቅርበት አንከታተላለን የሚሉ የደቡብ ኮርያ ባለስልጣኖች ዜናው ያልተጨበጠ እና ሰውዬውም በቅርቡ ጉብኝት ሲያደርጉ መታየታቸውን ገልፀዋል።
በሰሜን ኮርያ በኩል በጉዳዩ ላይ እስከ አሁን የተሰጠ ምላሽ የለም።