አሜሪካዊያን እና ኢትዮጵያን የጥቁር ህዝብ ታሪክ ወርን በአዲስ አበባ ማክበር ጀመሩ

ጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊያን እና ኢትዮጵያዊያን የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ወርን ምክንያት የፓናል ውይይት አድርገዋል፡፡

የጥቁር  ህዝቦች ሉዓላዊነት መከበር መነሻ በሆነችዉ ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ወር እየተከበረ ነው፡፡ 

ጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊያን በአለም ላይያደረጓቸዉን በጎ አስተዋጾዎች እና ያኖሯቸዉን አሻራዎችለመዘከር አላማ ያደረገዉ ክብረ በዓል ከኢትዮጵያዊያን ጋርበተለያዩ ፕሮግራሞች እያከበሩት ይገኛል፡፡

ጥቁር አሜሪካዊያኑ በተለያየ ዘርፍ ከተሰማሩ ኢትዮጵያዊያንጋር ያደረጉት የፓናል ዉይይት በኤሊያና ሆቴል ተካሂዷል፡፡ በፓናልዉይይቱ ላይ በተለያዩ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊምሁራን፣ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን፣  ዲፕሎማቶች፣ ኢትዮጵያዊስራ ፈጣሪዎችና ምሁራን ተሳትፈዉበታል፡፡ 

ጥቁር አሜሪካዊያኑ በተለይ በሃገረ አሜሪካ ለጥቁር ህዝቦችነጻነት ለማስከበር የተከፈለዉ መስዋትነት ትልቅ እንደሆነናአሁንም በስርአት የታገዘ ዘረኝነት በዓለም ላይ እንዳለ ተናግረዋል፡፡

የጥቁር ህዝቦች ሉዓላዊነትን ለማስከበር እና የጥቁሮችንልዕልና ከፍ ለማድረግ በዓለም ላይ ያሉ ጥቁሮች በጋራ መቆምእንዳለባቸዉም በፓናል ዉይይቱ ተነስቷል፡፡ 

ቀጣዩ ትውልድ እጣ ፈንታው እርስ በእርስ የተሳሰረ እንዲሆንከወዲሁ የዓለምን አወቃቀር ስርአት ተመልክቶ መገመት ይቻላል ያሉት ተወያዮቹ ትውልዱን በቴክኖሎጂ፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ማህበረሰብ ተኮር በሆነ ዘመናዊ ትምህርትበማገዝ በራሱ የሚተማመን ትውልድ መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡

የደቡብ ሱዳኑ አምባሳደር፣ የተለያዩ ዘርፍ ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪየሆኑ አፍሪካ አሜሪካዊያ ሴቶች እና ኢትዮጵያዊ ውጤታማ የሆኑ ሥራ ፈጣሪዎች ሴቶች ጥቁር ሴቶች ልዕልና ይችላሉበሚል የተሞክሮ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

28 አፍሪካ አሜሪካዊያን ተፅእኖ ፈጣሪ ሴቶችን በመዘከርለመጀመሪያ ግዜ ከአፍሪካ በኢትዮጵያ የተከበረው የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ወር የጥቁር ሉዓላዊነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ቆይቷል፡፡ክብረ በዓሉ በኢትዮጵያ በየዓመቱ መከበሩን እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *