ቶታል በአፍሪካ የመጀመርያው የሆነውን ቶታል ኳርተዝ የተባለ አዲስ የመኪና የዘይት ጀሪካኑን በኢትዮጵያ ላይ” ሀ” ብሎ ለገበያ ማቅረቡን መጀመሩን ደንበኞቹን ጠርቶ ዛሬ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል አስተዋውቋል።
አዲሱ የዘይት ጀሪካን አርጅቶ ቢጣል እንኳን አካባቢን ብዙ የማይበክል ለአያየዝ ቀላል የሆነ፣የዘይቱን አጠቃቀም የሚያሳይ በምስል የተደገፈ ማብራሪያ በጀሪካኑ ጎን ክፍሎች ላይ አስፍሯል። በተጨማሪም አዱሱ ጀሪካን የዘይቱን ምርት እውነተኛ የቶታል ምርት መሆኑን የሚያሳይ የ QR ኮድ ተለጥፎበታል።
ቶታል ላለፉት 70 አመታት በኢትዮጵያ ላይ በነዳጅና በመኪና ዘይቶች ሽያጭ ላይ አየሰራ ያለ የፈረንሳይ ኩባንያ ነው።